ትሪክ አይሽሬው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከእሁዱ የ 2025 ለንደን ማራቶን ውድድር ውጪ መሆኑን አዘጋጆቹ ይፋ አድርገዋል።
አትሌቲ ቀነኒሳ በቀለ በጉዳት ምክንያት በለንደን ማራቶን ውድድር መሳተፍ እንደማይችል አዘጋጆቹ እንዳሳወቃቸው ገልጸዋል።
ቀነኒሳ በቀለ በሰጠው አስተያየትም “ በእሁዱ የለንደን ማራቶን ወደ ውድድር ለመመለስ ጓጉቼ ነበር ባለመሳካቱ በጣም ተበሳጭቻለሁ “ ብሏል።
ከውድድሩ ውጪ የሆነው በጉዳት መሆኑን ያረጋገጠው ቀነኒሳ በውድድሩ ለሚካፈሉ አትሌቶች መልካም ምኞቱን ገልጿል።
@Tikvahethsport
