በአይነቱ ለየት ያለ ኮንሰርት ሽር ጉድ ኢንተርቴመንት ይህ የሙዚቃ ኮንሰርት በአጋጣሚዎች የተሞላ ቢሆንም እንዲህ አይነት ኮንሰርት ለማዘጋጀት ቀድሞ ያለመ እና ከተናፋቂው የሙዚቃ ወዳጅ ህዝብ ጋር ለማገኘት እያሰበ መሆኑን እና ከጉጉት ጋር ተያይዞ ነው፡፡
ሽር GOOD ኢንተርቴመንት ተቋም ዘለግ ያሉ ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በበርካታ ኮንሰርቶች በተባባሪ አዘጋጅነት ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ይሁን እና አሁን ካካበተው ልምድ እና ተሞክሮ አንድፃር ከተባባሪ አዘጋጅነት ወደ ዋና አዘጋጅነት በመሸጋገር የመጀመርያ ኮንሰርቱን ሽር GOOD በሚል ርዕስ ለማዘጋጀት ሽር ጉድ እያለ ይገኛል፡፡
ሽር- GOOD ከዚህ በኃላ የተለያዩ በእድቅ ደረጃ የያዛቸውን ስራዎች ለማከናወን እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ በቅርብ ታዋቂ አርቲስቶች የሚያሳትፍበት ተከታታይ የቴሌዢዥን ድራማ በማዘጋጀት ወደ መጠናቀቁ እየቀረበ መሆን ገልጿል፡፡
ሽር GOOD በይበልጥ በሙዚቃ ኢንደርስትሪው ላይ በስፋት ለመስራት እንዳሰበ ዛሬ ማክሰኞ 14/2017 በራማዳ ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿ፡፡ በተጨማሪም ታዋቂ አርቲስቶች ከ አዳዲስ ባለ ተስዖጦች ጋር በአንድ አገኛኝቶ ለማዘጋጀት እንደ እቅድም ይዟል፡፡
በአሁኑ ሰዓት በጉጉት የሚጠበቀው ቅዳሜ ሚያዝያ 18/2018 አመተ ምህረት የሚደረገው ታላላቅ የኪነጥበብ ሰዎችን የሙዚቃው ኢንደስትሪ ቆንጮዎቹን ለዘመን ማስታወሻ እና አይረሴ ትዝታን ለመከተብ በወርቃማ ብዕር ለማፃፍ ከድምፃዊያኖች ጋር ሽር ጉድ ኢንተርቴመንት ሽር ጉድ እያለ ይገኛል፡፡
አንጋፋ ድምፃዊያኖች አለማየሁ ሂርጶ እና ጎሳዬ ተስፋዬ(ኢቫንጋዲ) የዘጠናዎቹ ፈርጥ የጥምረት ምልክቶችን ከሀያ ዓመት በኃላ ዳግም በአዲስአበባ ሰማይ ስር በሚልየም አዳራሽ ይገናኛሉ፡፡ በተጨማሪ እውቁ የሙዚቃው ጥግ የትዝታ መንፈስ የሚጠራ ተወዳጁ ድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩ ይገኝበታል፡፡ የወጣቶቹን ልብ በጊዜ ያሸነፈችሁ ወጣትዋ ድምፃዊት ሜላት ቀለም ወርቅ የኮንሰርቱ አድማቂ ጌጥ ሆና በዝግጅቱ ትደምቃለች፡፡
የሽርጉድ ስራ አስኪያጅ እና ባለቤት የሆነው ተስፋዬ መንገሻ እንደ ገለፀው “ከዚህ በኃላም ኮንሰርት በማዘጋጀት አዳዲስ እና ወጣት ባለ ተስዕጦች ጋር ከነባሮች ጋር በማቆራኸት እቅድ ይዟል”ሲል ገልጿል፡፡ የሚልየም አዳራሽ የድግሱ መግብያ ከ 500( ከአምስት መቶ)-15,000(አስራ አምስትሺህ ብር ከምግብ ከመጠጥ ጋር አዘጋጅተዋል፡፡ በዚህ ታሪካዊ ቀን ማንም እንዳይቀር፡፡
via ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ
