ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት፣ ” በህዳሴ ላይ አንድም ብር እርዳታ፣ አንድም ብር ብድር ኢትዮጵያ አልወሰደችም ” ሲሉ ግልጽ ምላሽ ሰጥተዋል።
” በጀግኖች ኢትዮጵያውያን ቁርጠኛ አቋም በሀገር ውስም በከሀገር ውጭም ያሉ ኢትዮጵያውያን በቁርጠኝነት ጨከሰነው በጋራ ቆመው ስለሰሩ የተከወነ ፕሮጀክት ነው ” ሲሉም ተናግረዋል።
ዐቢይ (ዶ/ር) ይህን ያሉት ሜጋ ፕሮጀክቶች እምብዛም ስለሌሉ ወጣቶች ለስራ አጥነት ጨምር እየተጋለጡ በመሆኑ ለዚሁ ምላሽ እንዲጠሱ ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሲሰጡ ሲሆን፣ ” ከዚህ ንግግራቸው አስከትለውም፣ ” ግን በዚህ አላበቃም፤ ህዳሴ ከአፍሪካ አንደኛውን ሰርተናልና ሌላ አያስፈልግም እኮ አላለችም ኢትዮጵያ ” ብለዋል።
” በአፍሪካ ሦስተኛውንም ኮይሻ እየገነባን ነው ያለነው። የንፋሱን ሳንጨምር። በርካታ ፕሮጀክቶች ይሰራሉ ” ነው ያሉት።
” ‘ፕሮጀክቶ ቋሟል፤ ሜጋ፣ ሜጋ ፕሮጀክት የለም’ ለተባለው። እውነት ነው ፕሮጀክት የለም። ግን ከአፍሪካ አንደኛው ኤርፓርት ኢትዮጵያ ውስጥ ተጀምሯል። እንደዚህ ያለ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ አስባም ሰርታም አታውቅም” ሲሉ መልሰዋል።
” እውነት ነው ፕሮጀክት ቀንሷል የማዳበሪያ ፋብሪካ ኢትዮጵያ ውስጥ ተጀምሯል። ፕሮጀክት ቀንሷል የጋዝ ፌዝ ዋን ጨርሰን ፌዝ ቱ እና ሪፋይነሪ እየሰራን ነው ” ሲሉ በርካታ ግዙፍ ግዙፍ ፕሮጀክቶች እየተሰሩ መሆኑን አሳውቀዋል።
” በሜጋ ፕሮጀክት ፣ በፕሮጀክት ክትትል ፣ በፕሮጀክት አፈጻጸም ፣ በፕሮጀክት አመራር እንኳን ኢትዮጵያ ውስጥ ድፍን አፍሪካ ገና ከኢትዮጵያ ይማራል ” ብለዋል።
” ሰባት ቀን ቀን እና ማታ በየጥሻው ውስጥ የምንዞረው ፕሮጀክት ተጀምሮ ሳያልቅ እንዳይቆም ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።
