የህወሓት አንዳንድ ሰዎች ያላቸውን አቋም ሳይ ምን ያህል ህዝባቸውን እንደሚጠሉ እና የህዝባቸው በደል እንደማያማቸው ነው የገባኝ -ጠ/ ሚ ዐብይ አህመድ

Date:

እውነት ስላለን እና በቅንነት ህዝባችንን ማገልገል ስለምንፈልግ ማንም ድጋፍ ባይሰጠንም እውነተኛ ፈራጅ ስለሚያይ ማንም አያሸንፈንም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፡፡

ህወሓት በኤርትራ ወታደር እንዳይዘረፍ ስንጠብቀው አማራ ክልል ገብቶ ያደረገው ነገር አሳፋሪ ነው ሲሉ ኮንነዋል፡፡

ቡድኑ በአማራ ክልል ውስጥ ፋብሪካ ማፍረሱን፤ ትምህርት ቤት ማቃጠሉን እና ባንክ መዝረፉን አንስተዋል፡፡

የትግራይ ሀይል ይህንን በሚያደርግበት ወቅት ግን መከላከያ ሰራዊት መቀሌን ያለምንም ጥፋት ጠብቋታል ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ኢትዮጵያን ያላስቀደመ ለጊዜያዊ ድል እና ለሚዲያ ጨዋታ የሚደረግ የፖለቲካ ስብዕና በዘላቂነት በህዝብ እና በታሪክ ላይ ጉዳት ያመጣል ሲሉ ለምክር ቤት አባላት ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ በፕሪቶሪያ ስምምነት ወቅት የተስማማንባቸው ጉዳዮች ናቸዉ የፀብ መነሻ እየሆኑ ያሉት ያሉ ሲሆን፤ ይህ ሁኔታ ለማንም አይጠቅምም ብለዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...