በእስራኤልና ኢራን መካከል በተከሰተው ግጭትና በሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት ምክንያት ለወራት ጉዞዋ ተስተጓጉሎ የቆየችው የኢትዮጵያ ንብረት የሆነችው “ኤምቪ ጊቤ” መርከብ፣ በአሁኑ ወቅት ወደ ጅቡቲ ማቅናት መጀመሯን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አስታውቋል።
በአሁኑ ወቅት በኦማን ባሕረ ሰላጤ አካባቢ የምትገኘው ይህቺ ታሪካዊ መርከብ፣ ያጋጠማትን አስቸጋሪ እገታ በሰላም ተሻግራ ወደ መዳረሻዋ ለመድረስ በመጓዝ ላይ ትገኛለች።
የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በ347 ዓለም አቀፍ የወደብ መዳረሻዎች ላይ ከሚያውለበልቡ የሀገሪቱ የኩራት ምልክቶች አንዷ የሆነችው “ኤምቪ ጊቤ”፣ እ.ኤ.አ ሰኔ 28 ከምሽቱ 2:00 አካባቢ ጅቡቲ ወደብ ትደርሳለች ተብሎ ይጠበቃል።
