በምሥራቅ አፍሪካ የሚስተዋሉ ሽብርተኝነትንና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመከላከል የቀጣናው ሀገራት የመረጃ ትብብር ወሳኝ ነው

Date:

በምሥራቅ አፍሪካ የሚስተዋሉ ሽብርተኝነትንና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመከላከል የቀጣናው ሀገራት የመረጃ ትብብር ወሳኝ መሆኑን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ታዜር ገብረእግዚአብሔር ገለጹ።

የአፍሪካ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ኮሚቴ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ታዜር ገብረእግዚአብሔር በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ መድረኩ በመረጃ ትብብር የቀጣናውን ደህንነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ይመክራል።

ሽብርተኝነት፣ ጽንፈኝነት እና ሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ዛሬም ድረስ የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ስጋት ሆነው መቀጠላቸውን ገልጸዋል።

በመሆኑም በቀጣናው ያለውን የደህንነት ስጋት በመቆጣጠር ሰላም ለማስፈን በሀገራት መካከል የተቀናጀ የመረጃ ትብብር ያስፈልጋል ብለዋል።

የምሥራቅ አፍሪካ የመረጃና ደህንነት ተቋማት ስብሰባ፥ ቀጣናዊ ትብብሩ በተግባር የሚፈጸምበትን እድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

የጸጥታ ስራ የጋራ ትብብርን የሚጠይቅ ነው ያሉት አቶ ታዜር፤ ተቋማቱ ፈጠራን የተከተለና የህግ ማዕቀፍን ታሳቢ ያደረገ ቅንጅት መፍጠር አለባቸው ብለዋል።

የአፍሪካ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ኮሚቴ ዋና ፀሐፊ ጃክሰን ሀማታ በበኩላቸው፣ የአፍሪካ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ኮሚቴ ዓላማው የቀጣናውን ደህንነት በጋራ ለመጠበቅ ትብብርን መፍጠር መሆኑን ገልጸዋል።

የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት በመረጃ ላይ የተመሰረተ ቅንጅት በመፍጠር ሽብርተኝነትንና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን መከላከል እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 9 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን እንግዳ አምዳችን :- ‹‹ምንጩና ጸሐፊው በማይታወቅ መረጃ መመራት አደገኛ...

ሸኽ መሃመድ አል አሙዲ ተጨማሪ 40 ሺህ ሠራተኞች እንዲቀጠሩ አቅጣጫ ሰጡ

የMIDROC Investment Group ሊቀመንበር ሼክ መሃመድ ሁሴን አል...

የወርቅ ማዕድን ሠራተኛው ከመገደላቸው በፊት ቤተሰባቸው ከታጣቂዎች ጋር ያደረገው የመጨረሻው የስልክ ምልልስ

ማስጠንቀቂያ፡ ቀጥሎ የሚያነብቡት ታሪክ ሊረብሽዎት ይችላል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ...