በምሥራቅ አፍሪካ የውኃ ዋጋ በ2000% ጨመረ

Date:

በኢትዮጵያ፣ በኬንያ እና በሶማሊያ የተከሰተው አስከፊ የድርቅ አደጋ በአሁኑ ወቅት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለከፋ የረሃብ አደጋ ማጋለጡን ኦክስፋም አስታወቀ።

ድርቁ በተለይም የውኃ ዋጋ በአንዳንድ አካባቢዎች እስከ 2000 በመቶ እንዲንር በማድረጉ፣ በሦስቱ አገራት 26 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ለከፍተኛ ረሃብ መጋለጣቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ከ58 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ንጹሕ የመጠጥ ውኃ ያጡ ሲሆን፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የቤት እንስሳትም በድርቁ ምክንያት እያለቁ ይገኛሉ።

የውኃ ቀውሱና የዋጋ ንረቱ ማኅበረሰቡን ለከፍተኛ ምስቅልቅል ዳርጎታል። እንደ ኦክስፋም መግለጫ፣ ከጥቅምት እስከ ታኅሣሥ ባለው ጊዜ ሊዘንብ የነበረው ዝናብ በመቅረቱ የውኃ ጉድጓዶች በከፍተኛ ሁኔታ ደርቀዋል።

ይህም በሶማሊያ አንዳንድ አካባቢዎች ከአንድ ዓመት በፊት 0.06 ዶላር የነበረው አንድ ጄሪካን ውኃ አሁን እስከ 1.50 ዶላር እንዲሸጥ አድርጎታል።

የኦክስፋም አፍሪካ ዳይሬክተር ፋቲ ንዚ-ሀሳኔ እንደገለጹት፣ ሴቶችና ልጃገረዶች አንድ ጄሪካን ውኃ ለማግኘት እስከ 15 ኪሎ ሜትር በእግራቸው ለመጓዝ ተገድደዋል።

ዳይሬክተሯ አክለውም ለልጆቻቸው በቀን አንድ ጊዜ እንኳ ምግብ ማቅረብ ለማይችሉ ቤተሰቦች የውኃ ክፍያ የማይታሰብ ሆኗል ሲሉ አስረድተዋል።

እንደ ድርጅቱ ከሆነ በኢትዮጵያ ላለፉት ሁለት ወቅቶች ዝናብ ባለመዝነቡ ምክንያት የሰብል ምርት ከ34 እስከ 54 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል።

በሶማሊያ በረሃብ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 6.5 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ በ2025 ብቻ 1.4 ሚሊዮን እንስሳት አልቀዋል። በተመሳሳይ በኬንያ ሰሜናዊ ክፍሎች የእንስሳት ወተት ምርት ከግማሽ በላይ በመቀነሱ ቤተሰቦች ለምግብ እጥረት ተጋልጠዋል

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...

በሳዑዲ በምሕረት የተለቀቁ 320 ኢትዮጵያውያን

በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ከተሰጣቸው 1...