የአያቶላህ አሊ ኻሜኒን ተተኪ ለመሰየም ከስምምነት ላይ ተደረሰ

Date:

በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው መጠነ-ሰፊ ጦርነት ሁለተኛ ሳምንቱን ሲያስቆጥር፣ ቀጣናው ከዚህ ቀደም ታይቶ በማያውቅ የፖለቲካ ውጥረት ውስጥ ይገኛል።

አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ጥቃት መጠናከሩን ተከትሎ፣ የኢራን ከፍተኛ የሊቃውንት ጉባኤ የአያቶላህ አሊ ኻሜኒን ተተኪ ለመሰየም ከስምምነት ላይ መድረሱ ተሰምቷል።

ሆኖም እስራኤል መራጮችንም ሆነ ተመራጩን መሪ አድኖ ከመግደል ወደኋላ እንደማትል በይፋ በማስጠንቀቅ “የአደን” ዘመቻዋን ቀጥላለች።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በስምንት ቀናት ውስጥ 42 የኢራን የጦር መርከቦች መውደማቸውንና የአገሪቱ አየር ኃይል መዳከሙን ገልጸው፣ ጦርነቱ የሚቆመው ኢራን ያለ ቅድመ ሁኔታ እጅ ስትሰጥ ብቻ እንደሆነ በፅኑ አስታውቀዋል።

ግጭቱ ወደ ጎረቤት አገራትም በመስፋፋቱ በዱባይ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የድሮን ጥቃት የተፈጸመ ሲሆን፣ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማስዑድ ፔዜሽኪያን በስህተት ጥቃት ለደረሰባቸው ጎረቤቶች ይቅርታ ጠይቀዋል።

በአንጻሩ አሜሪካ የጦር መሣሪያ ምርቷን በአራት እጥፍ ለማሳደግ ስምምነት ላይ የደረሰች ሲሆን፣ የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሁኔታው ከቁጥጥር ውጪ ሊወጣ እንደሚችል በማሳሰብ አስቸኳይ የዲፕሎማሲ ንግግር እንዲጀመር ጥሪ አቅርበዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...

በሳዑዲ በምሕረት የተለቀቁ 320 ኢትዮጵያውያን

በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ከተሰጣቸው 1...

አሜሪካ እና እስራኤል ደቡብ ሊባኖስን ለአገሪቱ ጦር የማስረከብ ዕቅድ

አሜሪካ ድጋፏን በሰጠችው ዕቅድ መሠረት እስራኤል እና ሊባኖስ፤ የደቡብ...

የመሬት ልማትና አስተዳደር በበጀት ዓመቱ 63 በመቶ ያህሉን ማሳካት አልቻለም

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሊገባደድ በተቃረበው በጀት ዓመት ለመሰብሰብ...