የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት 27ኛ ወሩን በያዘበት ወቅት በጀነራል ሃምዳን ዳጋሎ የሚመራው ጥምረት መንግስት መስርቼያለሁ ብሏል።
እራሱን TASIS ሲል የጠራው ጥምረት 15 አባላት ያሉት የፕሬዚዳንታዊ ምክር ቤት ያለው ሲሆን ጀነራል ሃምዳን ዳጋሎ በፕሬዚዳንትነት ይመሩታል።
በተጨማሪ ጥምረቱ መሐመድ ሃሰንን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መሾሙን ገልጿል።
ጥምረቱ አላማው በፍትህ እና ነፃነት ላይ የተመሰረተችን ሱዳን መገንባት መሆኑን ገልጿል።
በጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር ከወራት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር መሾሙ ይታወሳል።
በሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል የተመሰረተው ጥምረት ጠቅላይ ሚኒስትር ከመሾሙ በተጨማሪ ለክልሎችም አስተዳዳሪዎችን መድቧል።
አሁን ባለው ተመድን ጨምሮ ሃገራት በሱዳን ጦር ለተመደቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ካሚል እድሪስ መንግስት እውቅና የሰጡ ከወራት በፊት ተመድ ሌላ መንግስት መመስረት ጉዳቱ የከፋ እንደሚሆን ሲያስጠነቅቅ ነበር።
ሃገሪቷ በሁለት ኃይሎች ተከፋፍላ በምትመራው ሱዳን የሱዳን ጦር ለተመሰረተው መንግስት የሰጠው ይፋዊ ምላሽ የለም።
ሱዳን በ2023 ወደ እርስ በእርስ ጦርነት ከገባች በኋላ በጦርነቱ ከ13 ሚሊየን ሰዎች በላይ ሲፈናቀሉ ከ15,000 በላይ ሰዎችም መምታቸው ይታወሳል።
Source: Al Jazeera, DW
