በቂ የሙያ ስልጠና ባለመሰጠቱ በሠራተኞች ላይ አደጋ እየደረሰ ነው

Date:

ለሠራተኞች የሙያ ስልጠና ሳይሰጥ ወደ ሥራ እንዲሰማሩ መደረጋቸው ለአደጋ ተጋላጭ እንዲሆኑ እያደረጋቸው እንደሚገኝ የኢትጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

በተለያዩ የሥራ መስኮች ላይ በተሰማሩ ሠራተኞች ስለ ሚሰሩት የሥራ መስክ በቂ የሆነ የሙያ ስልጠና እንዲሰጣቸው ማድረግ ከተቋማት የሚጠበቅ ኃላፊነት የሚጠበቅ መሆኑን የተናገሩት በኮንፌዴሪሽኑ የውጭ እና የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አያሌው አህመድ ናቸው፡፡

በተደጋጋሚ ሠራተኞች የተለያየ ጉዳት እየደረሰባቸው መሆኑን አንስተው፤ የሥራ ቦታቸው ከኬሚካል ጋር ግንኙነት ባላቸው ሠራተኞች ለጉዳቱ የበለጠ ተጋላጭ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የሥራ የደህንነት መስፈርቶች ባለመሟላታቸው የሚደርሱ ጉዳቶች በዜጎችን ሕይወት ላይ ጫና እያሳደረ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፤ ሠራተኞች የሥራ ላይ ደህንነትን በተሟላ ሁኔታ ባለመከተላቸው ምክንያት ሕወታቸው እያለፈ እና ለአካል ጉዳት እየተዳረጉ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በሥራ ቦታ ላይ ያለው የሥራ ደህንነት መስፈር በተመለከተ ክትትል የማያካሄድ ኃላፊነት ያለው የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ቢሆንም፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ችግሩን በብቸኝነት ሊፈታ ባለመቻሉ ሁሉም ባለ ድርሻ የበኩሉን ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል ።


ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...

አዲስ አበባ፦ የዜጎች ቀይ መስመር!

(የግል አስተያየት) አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መናገሻ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች ለዘመናት...

አብን የምክክሩን ውጤት ውድቅ አደረገ!

አብን በሀገራዊ ምክክሩ ማጠቃለያ ላይ የተፈጸመውን “ሕገ-ወጥ ጣልቃ-ገብነት” በመቃወም...