በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በአቶ ዮሐንስ ላይ የተፈረደባቸው ዉሳኔ ፓርቲያቸው “ፖለቲካዊ” ነዉ ብሎታል

Date:

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሕገ መንግሥት ማሻሻያ ላይ አቤቱታ ካቀረቡ በኋላ በቁጥጥር ስር የዋሉት በክልሉ ምክር ቤት የተቃዋሚው ቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ) ተመራጭ አቶ ዮሐንስ ተሰማ፤ የአምስት ዓመት ከ10 ወር ጽኑ እስራት እና የ15 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንደተፈረደባቸው አንድ የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራር ለአዲስ ስታንዳርድ አረጋገጡ።

የአሶሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአቶ ዮሐንስ ላይ የቅጣት ውሳኔውን ያስተላለፈው ከአምስት ዓመት በፊት ተቋርጦ በነበረው “ከሊዝ አዋጅ የከተማ መሬት አስፋፍቶ በመያዝ” ክስ መሆኑን እኚህ አመራር ገልጸዋል።

ቀደም ሲል በ2011 ዓ.ም በፖለቲካ ምክንያት እሳቸውን ጨምሮ [አቶ ዮሐንስን] ተይዘን ነበረ ያሉት አመራሩ በ2012 ዓ.ም ክሱ ተቋርጦ እንደነበረ አስታውሰዋል።

ይሁን እንጂ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሕገ መንግሥት ማሻሻያ ላይ አቤቱታ ካቀረቡ በኋላ “በሽብር እና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን በማፍረስ” በሚል በክልሉ የምክር ቤት አባልነታቸው የነበራቸው ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ በቁጥጥር ውስጥ መዋላቸውን አንስተዋል።

“ፖሊስም ሆነ አቃቤ ህግ በዚህ ክስ [በሽብር] መረጃ በማጣታቸው የተነሳ ከዚህ ቀደም ተከሰውበት እና ተቋርጦ የነበረውን ከሊዝ አዋጁ ጋር ተያይዞ የቀረበባቸውን ክስ እንዲቀጥል ተደርጓል” የሚሉት አመራሩ ፍርድ ቤት ሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ጥፋተኛ ተብለው በትናንትናው ዕለት የመጨረሻ ውሳኔ እንደተሰጠበት አመልክተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሴቶችን በቤት ውስጥ በማገዝ  መልካም ማህበረሰብ መፍጠር ተጀምሯል

በቤት ውስጥ የሚሠሩ ተግባራትን ተከፋፍሎ በመሥራት ሴቶችና እናቶችን መደገፍ...

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...