በብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ከ710 ሚሊዮን ዶላር በላይ ፍላጎት የቀረበበት መሆኑ ተገለጸ

Date:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባካሄደው የ500 ሚሊዮን ዶላር ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ከንግድ ባንኮች የ710 ሚሊዮን ዶላር ከፍተኛ ፍላጎት መቅረቡን አስታወቀ።

በዚሁ ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. በተካሄደው የገንዘብ ፖሊሲ ትግበራ ልዩ ጨረታ፣ ከተሳተፉት 22 ንግድ ባንኮች ውስጥ 21ዱ የዶላር ድልድል ማግኘት ችለዋል። የቀረበው የፍላጎት መጠን ባንኩ ለሽያጭ ካቀረበው በ210.14 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ ያለው ሲሆን፣ ይህም የ142 በመቶ ያህል ከፍተኛ ፍላጎት እንደነበር ያሳያል።

በዚሁ መሰረት ማዕከላዊ ባንኩ ባከናወነዉ ጨረታው የአንድ ዶላር አማካኝ ዋጋ  160.21 ብር ሆኖ ተመዝግቧል። ይህም ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ከተካሄደው መደበኛ ጨረታ (161.80 ብር) ጋር ሲነጻጸር የብር የመግዛት አቅም በአንድ በመቶ ገደማ ከዶላር አንፃር ተጠናክሯል።

ይህ ልዩ ጨረታ ብሔራዊ ባንክ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ለማካሄድ ካቀዳቸው አራት መደበኛ የ125 ሚሊዮን ዶላር ጨረታዎች ውጪ የተካሄደ ሲሆን፣ ቀጣዩ መደበኛ ጨረታ በነሐሴ 20 ቀን ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...

«ግብጽ ዛቻውን አቁማ ወደ ድርድር ትግባ!»

ታዋቂው የአፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝ ዶ/ር ዴቪድ ማትሳንጋ ግብጽ በኢትዮጵያ...