በታራሚዎች አያያዝ ዙሪያ አቤቱታ የቀረበባቸው ማረሚያ ቤቶች ላይ ምርመራ እየተደረገ ነው

Date:

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ኦሮሚያ ቅርንጫፍ በክልል ባሉ ማረሚያ ቤት አስተዳደሮችላይ የቀረቡለትን አቤቱታዎች በተመለከተ ምርመራ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ለአራዳ ገልጿል።

በህግ የተሰጡንን አገልግሎቶችየማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ከልክሎናል የሚሉ ቅሬታዎች የደረሰው ተቋሙ፥ ምርመራው ሲጠናቀቅ ውጤቱን ይፋ እንደሚያደርግ ነው የጠቆመው።

ለአንድ ታራሚ በቀን በተበጀተለት መሰረት እየተፈፀመለት መሆኑንና ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ችግሮች አለመኖራቸውን ማጣራት የምርመራው አካል መሆናቸውንየተቋሙ ኃላፊ ደረጄ ተክሌ ለጣቢያችን አስረድተዋል።

በተለይም ምርመራው እስከሚጠናቀቅ ስማቸው የማይገለፅ በክልሉ የሚገኙ ሁለት ማረሚያ ቤቶች የታራሚዎችን ዴሞክራሲያዊ መብቶችበመንፈግ ከፍተኛ የሆነ ቅሬታ የቀረበባቸው ናቸው ብለዋል።

ኃላፊው በጥቅሉ ባለፈው በጀት ዓመት ይህንን ጨምሮ 1 ሺህ 330 የሚሆኑ ሰዎች የተካተቱበት 179 የአቤቱታ መዝገብ የቀረበ ሲሆን 65 መዝገብ ተቀባይነትእንዳገኘ ተናግረዋል።

ተቋሙ በእቅዱ ልክ አቤቱታዎች እየቀረቡለት እንዳልሆነና ዜጎች በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞና በትግርኛ ቋንቋዎች ቅሬታቸውን በ9503 ነፃ የስልክ መስመር እንዲያደርሱ ጥሪ አቅርቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...

ኧረ ፋታ ስጡን?!

መንግስት ግን" ምን ሁኑ ?" ሊለን ነው :: አጀንዳ...