ለአትሌት አበበ ቢቂላ በጃፓን ካሳማ ከተማ መንገድ ተሰየመ

Date:

በጃፓን ካሳማ ከተማ በአበበ ቢቂላ ሥም ግማሽ ማራቶን የሚካሄድበት መንገድ መሰየሙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ይህም መንገዱን በአትሌቱ ሥም የመሰየም ስነ-ሥርዓት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሃደራ አበራ፣ በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳድር ዳባ ደበሌ እንዲሁም የካሳማ ከተማ ከንቲባ በተገኙበት ተከናውኗል።

ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ይህ ታላቅ በዓል ለታዋቂው ኢትዮጵያዊ አትሌት ክብር ከመስጠት በተጨማሪም በኢትዮጵያ እና በጃፓን መካከል ያለውን ዘላቂ ወዳጅነት እና የባህል ትስስር ማሳያም ሆኖ እንደሚያገለግል ገልጸዋል።

አትሌት አበበ ቢቂላ በ1964 ቶክዮ ኦሎፒክ ድል ላይ ኢትዮጵያ ከፍ እንድትል ከማስቻሉ በተጨማሪ በሁለቱ አገራት ግንኙት አሻራውን ማስቀመጥ መቻሉን አመላክተዋል።

አምሳደር ደባ ደበሌ በበኩላቸው፤ ቀኑን ኢትዮጵያን እና ጃፓንያውያን ለዘመናት የሚያስታውሱት መሆኑን ገልጸው፣ አትሌት አበበ ቢቂላ በጃፓን የተጎናፀፈው ድል የጃፓን ማህበረሰብ ውስጥ ትልቅ ቦታ እንዳለው ተናግረዋል።

የካሳማ ከተማ ከንቲባ ሻንጁ ያማጉቺ ይህ መታሰቢያ በሁለቱ አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው መናገራቸውን አሐዱ ከሚኒስቴሩ ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

(አሐዱ ሬዲዮ) ‎

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምንገድ ላይ

(በእውቀቱ ስዩም) በቀደም ከሆነ ቦታ ተነስቼ ወደ አልሆነ ቦታ ስራመድ...

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ...