“የባሕር በር ካለህ ዓለም ሁሉ ገበያህ ነው”

Date:

የኢኮኖሚ ጫና ያለባቸው ሀገራት የባሕር በር አማራጭ ከሌላቸው በልማት ማነቆዎች የተጠፈነጉ እንደሚሆኑ የምጣኔ ሀብት እና የሕዝብ ፖሊሲ ፕሮፌሰር የሆኑት ፖል ኮሊየር ይገልፃሉ።

“የባሕር በር ካለ ዓለም ሁሉ ገበያህ ነው፤ ከሌለ ግን ከጥቂቶች ጋር ብቻ ትገበያያለህ” በማለት ሃሳባቸውን ያስቀምጣሉ፤ ይህንኑ ሃሳብም በርካቶች ይስማሙበታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “በቀይ ባሕር ዙሪያ ያሉ የጎረቤት ሀገራትን ሉዓላዊነት እናከብራለን፤ ነገር ግን ኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሀገር ሆና እንድትቀጥል የባሕር በር እንደሚያስፈልጋት እነርሱም ሊያምኑ እና ሊያከብሩ ይገባል” ሲሉ መናገራቸው የሚታወስ ነው።

በታሪክ ብሎም በሕግ የባሕር በር አማራጭ የማግኘት መብት ያላት ኢትዮጵያ፣ ቀይ ባሕርን የማስተዳደር ተሳታፊነት ላይ ልትካተት ይገባል የሚሉት የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ተመራማሪ አበራ ሃኢብሳ ናቸው።

ተመራማሪው ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ በምስራቅ አፍሪካ ቀንድ ያለው መረጋጋት እና ሰላም ዘላቂ እንዲሆን በማድረግ ሂደት ውስጥ ኢትዮጵያ የባሕር በር አማራጭ እንድታገኝ መስራት አስፈላጊ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ያላትን ሀገር ቆልፎ ማቆየት አግባብ እንዳልሆነ በመግለፅ፤ ይህንንም ለማስቀረት የትውልዱን ጥያቄ ማስመለስ ይገባል ሲሉ ያስረዳሉ፡፡

የፖለቲካ ተመራማሪው አስራት ኤርሜሎ በበኩላቸው፤ በኢኮኖሚ ለመጠንከር ማምረት ብቻ ሳይሆን የተመረተውን ወደ ወጪ የገበያ ንግድ የሚቀርብበት አማራጭ ያስፈልጋል ይላሉ፡፡

አክለውም ሉዓላዊነትን በማጎልበት በባሕር በር ጉዳይ መነጋገርና እና ተጠቃሚነትን ማሳደግ አማራጭ የሌለው ምርጫ ነው ብለዋል፡፡

EBC

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...

በሳዑዲ በምሕረት የተለቀቁ 320 ኢትዮጵያውያን

በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ከተሰጣቸው 1...

አሜሪካ እና እስራኤል ደቡብ ሊባኖስን ለአገሪቱ ጦር የማስረከብ ዕቅድ

አሜሪካ ድጋፏን በሰጠችው ዕቅድ መሠረት እስራኤል እና ሊባኖስ፤ የደቡብ...

የመሬት ልማትና አስተዳደር በበጀት ዓመቱ 63 በመቶ ያህሉን ማሳካት አልቻለም

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሊገባደድ በተቃረበው በጀት ዓመት ለመሰብሰብ...