በትግራይ ክልል የኤች አይ ቪ ቫይረስ ስርጭት 3 በመቶ ደርሷል ተባለ

Date:

በትግራይ ክልል ኤች አይ ቪ ቫይረስ ከነበረበት ደረጃ ወደ 1.42 በመቶ ቀንሶ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ የበሽታ ስርጭቱ 3 በመቶ መድረሱን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡

ከጦርነቱ በኋላ በቅርቡ በተካሄደው ጥናት የ ስርጭቱ መጠን ሴተኛ አዳሪዎች ላይ 8.5 በመቶ እንዲሁም ተፈናቃዮች ላይ ወደ 5.5 በመቶ መሆኑን በትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የኤች አይ ቪ ኤድስ ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ፍሰሀ ብርሀነ ተናግረዋል፡፡

ለስርጭቱ መጨመር በሰአቱ የነበረው የመድሀኒት አቅርቦት እጥረት እና የኮንዶም አቅርቦት አለመኖር በዋናነት ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል፡፡

እንዲሁም ስለ ኤች አይ ቪ ያለው ግንዛቤ እጅግ አናሳ መሆኑ ሌላኛው ምክኒያት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

አሁን ላይ ግን አልፎ አልፎ መቆራረጦች ቢኖሩም የመድሀኒት አቅርቦት እጥረት አለመኖኑን ዳይሬክተሩ አንስተዋል፡፡

አሁን ላይ ኤች አይ ቪ ኤድስ አደጋ መሆኑን ህብረተሰቡ ሊገነዘብ እንደሚገባ እና እያንዳንዱ ግለሰብ ከቤቱ ጀምሮ ስለ በሽታው ማወቅ እንዳለበት የገለጹት ሃላፊው የሃይማኖት ተቁዋማትን ጨምሮ ስለበሽታው ግንዛቤ በመፍጠሩ በኩል ሁሉም አካል ሃላፊነቱን እንዲወጣ የሚል መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...