በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ዳግም ጦርነትእንዳይቀሰቀስ ዲፕሎማቶች አሳሰቡ

Date:

በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ዳግም ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ከወዲሁ መግታት እንደሚገባ የአሜሪካና አውሮፓ ዲፕሎማቶች አሳሰቡ፡፡

የአፍሪካ ቀንድ ምክትል ልዩ መልዕክተኛ የነበሩት ፓይተን ኖፍ እና የቀይ ባህር የጥናት ማዕከል ሊቀመንበር አሌክሳንደር ሮንዶስ፣ በሁለቱ ጎረቤት ሀገራት መካከል የሚስተዋለውን ውጥረት አስመልክተው፣ ፎሬይን ፖሊሲ መጽሔት ላይ ሀሳባቸውን አጋርተዋል፡፡

በሁለቱም በኩል የሚስተዋሉ የቃላት ልውውጦችና የጦርነት ዝግጅቶች በሀገራቱ መካከል ጦርነት ሊቀሰቀስ እንደሚችል አመላካች እንደሆኑ ዲፕሎማቶቹ ጠቁመዋል፡፡

በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ያለው ፍጥጫ ወደ ጦርነት የሚያድግ ከሆነ ሰሜን ምስራቅ አፍሪካንና በጂኦፖለቲካዊ ጠቀሜታው ወሳኝ የሆነው ቀይ ባህር ላይም ችግር ሊጋርጥ እንደሚችል አመልክተዋል፡፡

አለም በሰፊ አህጉራዊና አለምአቀፋዊ ስርዓት አልበኝነት እየተናጠች በምትገኝበት በዚህ ወቅት፣ በትግራይ ያለው የፖለቲካና የጸጥታ ሁኔታ መበላሸት በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ጦርነትን ሊያስከትል እንደሚችልም አሳስበዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...