በኦሮሚያ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች የትርፍ ሰዓት በአዲሱ የደመወዝ እንዲሰላ ጠየቁ

Date:

በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች የክልሉ መንግሥት የትርፍ ሰዓት ክፍያዎችን በቅርቡ በተደረገው የደመወዝ ማሻሻያ መሠረት እንዲያሰላ ጠየቁ። ባለሙያዎቹ ጥያቄውን ያቀረቡት የፌዴራል መንግሥት በመላ ሀገሪቱ ወጥ የሆነ የክፍያ ሥርዓት እንዲኖር ካወጣው መመሪያ ጋር በተጣጣመ መልኩ እንዲተገበር መሆኑ ተገልጿል።

በባሌ ሮቤ አጠቃላይ ሆስፒታል የሚገኝ አንድ የጤና ባለሙያ ለአዲስ ስታንዳርድ፣ ጥያቄያቸው የተሻሻለውን የደመወዝ መዋቅር መሠረት በማድረግ የሚከናወኑ የሥራ ክፍያዎችን የሚገዛውን ብሔራዊ መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል።

“ለአዲሱ የደመወዝ ማሻሻያ የሚሆን በጀት የለም ተብለናል። ለሁለት ወራት በአዲሱ ደመወዝ መሠረት የትርፍ ሰዓት ክፍያ አግኝተን ነበር፣ ከዚያ በኋላ ግን ክፍያው ተቋርጧል” ሲል ባለሙያው ተናግሯል።

በጉደር ሆስፒታል የሚገኝ አንድ ሐኪም በተመሳሳይ ሁኔታ የመስከረም እና ጥቅምት ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያዎች በአዲሱ ደመወዝ መሠረት መሰጠታቸውን ያረጋገጠ ሲሆን፣ ሆኖም የሆስፒታሉ አመራሮች በኋላ ላይ ተጠርተው ክፍያውን በ“በአዲሱ ደመወዝ” መሠረት እንዳይፈፀም መመሪያ እንደተሰጣቸው ሐኪሙ ገልጿል።

የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ኃላፊ ፕሮፌሰር ነፃነት ወርቅነህ ለአዲስ ስታንዳርድ በሰጡት ምላሽ፣ ውሳኔው በክልል ደረጃ የተላለፈ መሆኑን ገልጸው ስለ ዝርዝሩ ግን ተጨማሪ ማብራሪያ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

https://addisstandard.com/Amharic/?p=10507

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...