አነስተኛ ወርቅ አምራቾችን ወደ ኢንዱስትሪ መሪነት የማሸጋገር ሥራ እየተከናወነ ነው

Date:


በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አነስተኛ የወርቅ አምራቾችን ወደ ዘመናዊ የኢንዱስትሪ ባለቤትነት የሚያሸጋግር አሠራር በመዘርጋትና በቴክኖሎጂ በመደገፍ ወደ ኢንዱስትሪ መሪነት የማሸጋገር ሥራ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ማዕድን ልማት ቢሮ አስታወቀ።

የምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ናስር መሀመድ እንደገለጹት፤ በማዕድን ልማት ዘርፉ ለአካባቢው ነዋሪዎች ሰፊ የሥራ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ አነስተኛ አምራቾችን ወደ ዘመናዊ የኢንዱስትሪ ባለቤትነት የሚያሸጋግር ሥርዓት ተዘርግቷል።

አነስተኛ አምራቾችን በአምስት ሄክታር መሬት ላይ በማደራጀት ወደ ሥራ እንዲገቡ በተደረገው ጥረት እስካሁን ከ50 ሺህ በላይ ዜጎች ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን የገለጹት አቶ ናስር፤ ይህ አደረጃጀት የአካባቢው ነዋሪዎች ያላቸውን የቆየ ልምድና እውቀት ከሕጋዊ አሠራር ጋር በማቀናጀት ኑሯቸውን እንዲያሻሽሉ ዕድል መፍጠሩን ተናግረዋል።

አምራቾቹን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ወደ ተሻለ የኢንዱስትሪ ደረጃ የማሸጋገር ሥራ ትኩረት የተሰጠው ሲሆን፤ ባለሀብቶች ከአነስተኛ አምራቾች ጋር በጋራ እንዲሠሩ ወይም ከ5 እስከ 50 ሄክታር መሬት ወስደው በኩባንያ ደረጃ እንዲሰማሩ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።

ከወርቅ በተጨማሪ እንደ የድንጋይ ከሰል፣ እምነበረድ እና ብረት ያሉ 17 ዓይነት ማዕድናት ለክልሉ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ እንደ ሞተር እንዲያገለግሉ ጥናት እየተደረገባቸው እንደሚገኝም ምክትል ቢሮ ኃላፊው ጠቁመዋል።

ጋዜጣፕላስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...