በክልል እና በፌዴራል ደረጃ ያሉ ሁሉም የመንግስትና መኪናዎች ወደ ኤሌክትሪክ እንዲዞሩ  ተገለፀ

Date:

አውቶብሶችን፣ ባቡርንና ሌሎች የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶችን በስፋትና በአግባቡ መጠቀም፤ አገልግሎቱም በወጣለት ታሪፍና መርሃ-ግብር ያለ መቆራረጥ እንዲሰጥ ሚኒስቴር መ/ቤቱ  ጠይቋል፡፡

የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር “የኢትዮጵያን የትራንስፖርት ዘርፍ ወደ ኤሌክትሪክና የተፈጥሮ ጋዝ የማሸጋገር እና የነዳጅ ቁጠባ ሀገራዊ ጥሪ” በሚል ርዕስ መግለጫ አውጥቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት በመካከለኛው ምስራቅ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት የዓለም የነዳጅ ገበያ ከፍተኛ ጭማሪ እያሳየ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም በትናትናው ዕለት ባወጡት መግለጫ ‘’ነዳጅን በቁጠባ እንጠቀም’’ ሲሉ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴርም  ወቅታዊውን ዓለም አቀፍ ጫና ለመቋቋም እና የሀገርን ኢኮኖሚ በዘላቂነት ለመታደግ  ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል፣ በመንግስትና በግል ተቋማት ዘንድ ተግባራዊ እንዲደረጉ ብሎ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በነዳጅና በኤሌክትሪክ የሚሰሩ (Plug-in Hybrid) ተሽከርካሪዎች ነዳጅን በመተው የኤሌክትሪክ ኃይልን ብቻ እንዲጠቀሙ ማስቻል፤ እንዲሁም በነዳጅ የሚሰሩትን ወደ ኤሌክትሪክና ተፈጥሮ ጋዝ የመቀየርስራን ማጠናከር፤ እስከ 20 ቶን የሚጭኑ የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደ ኤሌክትሪክ፣ ከ20 ቶን በላይ የሆኑት ደግሞ ወደ ተፈጥሮ ጋዝና ኤሌክትሪክ እንዲቀየሩ መንግስትና የግሉ ዘርፍ በቅንጅት እንዲሰሩ  መ/ቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ከአንድ ቤት ውስጥ ብዙ መኪናዎችን ይዞ መንገድ ከመውጣት ይልቅ፣ በጋራ የመጠቀም ልምድን ማዳበርና ተግባራዊ ማድረግ፣በከተማ ውስጥ የሚደረጉ አጫጭር ጉዞዎችን በእግርና በብስክሌት የማድረግ ባህልን ማሳደግ ይገባል ሲልም ጥሪ አቅርቧል፡፡

የትብብር ጥሪው የሀገርን የውጭ ምንዛሬ ለማዳን፣ የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስና ዜጎች በዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ መዋዠቅ እንዳይጎዱ ለማድረግ የታለመ ነው ሲልም የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...