በውሳኔው መሠረት ኦሎምፒክን የሚመራው ማነው?በቀጣይ ምን ይሆናል?

Date:

📌የኢትዮጵያ ህዝብ በጉጉት ሲጠብቀው የነበረው እነ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴና አትሌት ገዛኸኝ አበራ በእነ ዶክተር አሸብርና በኦሎምፒክ ኮሚቴው ላይ የተመሠረተው ክስ ውሳኔ ተሠጠበት

📌አስቸኳይና መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተላለፉ ውሳኔዎችና በ2016 የተደረገው ህገወጥ የስራ አሰፈፃሚ ቦርድ ምርጫ እንዲታገድ ፍ/ቤት ተወስናል

📌ይነሳ የተባለው እግድ እንዲፀናም ተወስኗል

📌ንብረት፣በውጭ ምንዛሪም፣በኢትዮጵያ ብር ያለ ገንዘብ(አካውንት)በገለልተኛ አካል እንዲንቀሳቀስም ተወስኗል

📌በውሳኔው መሠረት ኦሎምፒክን የሚመራው ማነው?በቀጣይ ምን ይሆናል?

ዶ/ር አሸብርን ጨምሮ በ5 የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራሮች ከሕገ ወጥ ምርጫና ከህገወጥ የሰዎች ዝውውር ጋር በተያያዘ የተመሠረተው ክስ ለዓመታት ግራና ቀኙን ሲያከራክር ቆይቶ ፍ/ቤቱ ውሳኔ አስተላልፏል።

በኦሎምፒክ ፕሬዝዳንቱ ዶክተር አሸብርና በአምስት የኮሚቴ አመራሮች ክሱን የመሰረቱት :-ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ፣አትሌት ገዛኸኝ አበራ፣የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን እና የኢትዮጵያ ቴኒስ ፌዴሬሽን ናቸው።

“ግንቦት አምስት እና ሰኔ አራት ላይ የተደረጉት አስቸኳይ እና መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተወሰኑ ውሳኔዎች የኦሊምፒክ ኮሚቲውን ህግ እና ስርዓት ያልተከተሉ እና ሕገ ወጥ ስለሆኑ ተቀባይነት የላቸውም፣የመንግስት ሀብት አለአግባብ ባክኗል፣በውጪና በገለልተኛ ኦዲተር ኦዲት ይደረግ የሚሉና በህዝብ ገንዘበ በርካታ የማይመለከታቸው ሠዎች ከ137 ሠው በላይ በመንግስት ገንዘብ ወደ ፓሪስ እንዲሄዱ በዚህ ውስጥም ህገ-ወጥ የሠዎች ዝውውር ተካሂዷል ብለን እንጠረጥራለን በማለት ክስ መመስረታቸውና ለዓመታት በፍ/ቤት ሲከራከሩ መቆየታቸው ይታወሳል።

የፌዴራል ከፍተኛው ፍ/ቤት ጉዳዩን ሲመረሞር ቆይቶ በቀን 11/11/17 በወሠነውና በደብዳቤ በተገለፀው ውሳኔ መሠረት በኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት በዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ እና በሶስት የኮሚቴው አባላት ላይ የሚፀና ውሳኔ አስተላልፏል።
በውሳኔው መሠረት:-

1ኛ.“ግንቦት 5 እና ሰኔ 4 የተደረጉት አስቸኳይ እና መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተወሰኑ ውሳኔዎች የኦሊምፒክ ኮሚቲውን ህግ እና ስርዓት ያልተከተሉ እና ሕገ ወጥ ስለሆኑ እንዲሁም የስራ አስፈፃሚ ምርጫም ህጉን የተከተለ አይደለም በሚል ዶክተር አሸብርና ካቢኒያቸውን ለቀጣይ አራት አመታት ወደስልጣን ያመጣው ምርጫ እንዲታገድ ተወሠኗል

2ኛ.በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በሌሎች ባንኮች የተቀመጡ የውጪ ሃገር ገንዘቦችና የኢትዮጵያ ብር ተቀማጭና ተንቀሳቃሽ አካውንት ውስጥ የሚገኙ ሂሳብ(ገንዘብ) እንዲሁም ንብረቶች በኦሎምፒክ ኮሚቴ ሳይሆን በሁለቱም በሚመረጡ በገለልተኛ የንብረት አስተዳዳሪ አካላት እንዲንቀሳቀሱ ፍ/ቤት ወስናል።

ለዓመታት የስፖርቱን መንደር ሠላም የነሳውና የሀገሪቱ ስፖርት የደማንለት ነው ያገባና፣ህግ ሲጣስ፣ህገ-ወጥ ምርጫ ሲደረግ አናይም፣የመንግስት ሃብት ሲመዘበር፣ሲባክን ዝም ብለን አናይም ባሉት በእነ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴና አትሌት ገዛኸኝ አበራ ፊት መሪነት ምርጫው ህጋዊ ነው እሰከ ሎስአንጀለስ ኦሎምፒክ ከስልጣናችን የሚነቀንቀን የለም፣

የባከነም የተመዘበረ ሀብት የለም በሚል ሲካሄድ የነበረው ክርክር አሁን የመጨረሻ ዕልባት ያገኘ ይመስላል፤ይግባኝ የማለት መብቱ ተስጥቶ መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መዝገብ የተመለሰ ቢሆንም ማን የይግባኝ መብቱን ተጠቅሞ ዳግም የስፖርቱን መንደር ወደማያባራ ዳግም ክርክርና ክስ ይወስደው ይሆን የምናየው ይሆናል።

✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...