ዕውቁ ኢትዮጵያዊው ገጣሚ እና ደራሲ በዕውቀቱ ሥዩም በስፔን ባርሴሎና በተካሄደው ዓለም አቀፍ የሥነ ግጥም ፌስቲቫል ላይ የጥበብ ሥራዎቹን አቅርቧል።
በዕውቀቱ ከሁለት ዓመት በፊት በፓሪስ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተካሄደ ዝግጅት ላይ ያቀረበውን የግጥም ትዕይንት ለዚህኛው ዓለም አቀፍ መድረክ እንዲመረጥ ምክንያት ስለመሆኑ ተነግሯል።
ከበዕቀቱ ጋር ሌሎች ስድስት ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ገጣሚያን በፌስቲቫሉ የመዝጊያ ዝግጅት ላይ የጥበብ ሥራቸውን አቅርበዋል።
በዕውቀቱ በዚህ ከፍተኛ ቦታ በሚሰጠው ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ሥራዎቹን ማቅረቡ ለኢትዮጵያ የሥነ ግጥም ዘርፍ ከፍተኛ መነቃቃትና ዕውቅና የሚያስገኝ ስለመሆኑም አስተያየት ሰጪዎች ጠቁመዋል።
በመድረኩም “የውበት ጀርባው”፣ “እንደምትወዳት ንገራት”፣ “ዕንባዬን የት ላርገው”፣ “ኑረሽ እይው በቃ” የሚል አርዕስት ያላቸውን የግጥም ሥራዎቹን አቅርቧል ።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
