የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚንስትር ጌታቸው ረዳ TBS ከተባለ የቴሌቪዥን ጣብያ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር።
ከ90 ደቂቃ በላይ በነበራቸው ቆይታ በቅርቡ በፌደራል መንግስት ስለተሰጣቸው ሃላፊነትና ስለ ትግራዩ ጦርነትና ጦርነቱ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ካቆመ በኃላ በክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር የነበራቸው የፕሬዜዳንት ሃላፊነት አስመልክተው ተናግረዋል።
ሚንስትር ጌታቸው ረዳ በቅርቡ በፌደራል መንግስት ስለተሰጣቸው የስራ ሃላፊነት ምን አሉ ?
– ” ከትግራይ ተገፍቼ ወጥቼ ወደ ስደት እንዳልሄድ አገሬንና ህዝቤን የማገለግልበት እድል ነው የተሰጠኝ፤ ይህንን እድል እንዳገኝ ላመቻችሉኝ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር አመሰግናለሁ። “
– ” የአፍሪካ ቀንድ ሰላም መሆን ከቀጠናው አልፎ ለኢትዮጵያም እፎይታ ይሰጣል። “
– ” ዳግም ግጭት እንዳይቀሰቀስ የተቻለኝን ሁሉ እሰራለሁ። “
– ” አሁን በተሰጠኝ የሃላፊነት ቦታ በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላም እንዲኖር አማጥጬ እንድሰራ ከፍተኛ እድል ይፈጥርልኛል። “
– ” ከአሁን በፊት ግጭት እንዲፈጠር የነበረኝ ሚና ይበቃል ፤ አሁን በተመደብኩበት ቦታ በትግራይ ፣ በኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እንዲሰፈን በመስራት ያለፈውን ጥፋቴ ለማካካስ እሰራለሁ። “
ሚንስትር ጌታቸው ረዳ ወደ ሱዳን ስላደረጉት የመጀመሪያ ጉብኝት ምን አሉ?
– ” የፌደራል መንግስት በቅርቡ የሰጠኝ ሃላፊነት በመወከል የመጀመሪያ የሰላም መልእክት ለማድረስ ወደ ሰሜንና ደቡብ ሱዳን ተጉዣለሁ፤ ጉብኝት ውጤታማ ነበር። “
– ” የጠቅላይ ሚንስትሩ የሰላም መልእክት ለአል ብሩሃንና እንዲሁም ለሌሎች አመራሮች አደርሰናል። “
– ” በሰሜንና ደቡብ ሱዳን የሚታየው የሰላም እጦት እንዲያበቃ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ያላቸው ልባዊ ፍላጎት ለከፍተኛ አመራሮች አድርሰናል። “
– ” መገዳደል እንዲያቆሙ መክረናል። “
– ” ግጭት በማስወገድ የሃሳብ ልዩነት በሰላማዊ መንገድ በጠረጴዛ ማራመድና ማስተናገድ እንደሚቻል ለአገርና ለህዝብ መስራት እንደሚቻል የአገራችን ልምድ በመጥቀስ ነግረናቸዋል። “
– ” ከትግራዩ ግጭትና የግጭት አፈታት ትምህርት እንዲወስዱ ነግረናቸዋል። “
– ” ጆሴፍ ስታሊን ‘ አንድ ሰው ከገደልክ ወንጀል ነው ፤ ሁለት ሰው ከገደልክ ወንጀል ነው ፤ ሚሊዮን ሰው ከገደልክ ግን ቁጥር ነው ‘ ይላል ፓለቲከኞች ለሰው ህይወት ዋጋ መስጠት አለባቸው ፤ በወጣቶች ደም መነገድ ማብቃት አለበት የሚል መልእክት አስተላልፈናል። “
– ” በአከባቢው ያሉት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ድህንነት እንዲጠበቅ መልእክት አስተላልፈናል። “
ሚንስትሩ ስለ ትግራይ ፓለቲካ ምን አሉ ?
– ” ስልጣን እኔ ከያዝኩት ቅዱስ ነው ሌላ ከያዘው ርኩስ ነው የሚለው የፓለቲከኞች የእብደት አካሄድ መገራትና መቆም አለበት። “
– ” በዚህች አገር በጠመንጃ አፈሙዝ በመታገዝ ስልጣን ለመያዝ ማለም ማብቃት አለበት። “
– ” የትግራዩ ጦርነት ለክልሉም ሆነ ለአገሪቱም እንዲሁም ለአህጉራችን ትልቅ ትምህርት መሆን ይገባዋል። “
– ” ትግራይም ሆነች ኢትዮጵያ ካለፈው ግጭት ያተረፉት ምንም ነገር የለም። “
– ” የትግራይ ፕሬዜዳንት ሆኜ በሁኔታዎች አለመመቻቸት መስራት እያለብኝ ያልሰራሁት ብዙ ነው። “
– ” ትግራይ ተመልሼ መስራት መቐለ መኖርን ነው እምፈልገው። “
– ” የትግራይ ህዝብ ሰላምና ደህንነት እንዲጠበቅ አቅሜ አማጥጬ እሰራሎህ። “
– ” ወደ ህወሓት ከፍተኛ የአመራርነት ቦታ የጠቆመኝ እና ያመጣኝ ስብሃት ነጋ ነው። አንዳንድ የፓለቲካ ክፋቶች ከስብሃት ነጋ ነው የተማርኩት። “
– ” አሁን ያለው የህወሓት አመራር ከስህተቱ የማይማር ብቻ ሳይሆን ስህተቱ እንደ ሙያ ፕሮፌሽን የወሰደና የቆጠረ የደረቀ አመራር ነው። “
– ” ህወሓት 300 ሺህ አባላት አሉት በአመራር ግን የታደለ አይደለም። “
– ” የህወሓት አመራር ብቃት የለውም መቀየር አለበት ምክንያቱ ይህ ነው የሚባል የለውጥ ስትራቴጂ የለውምና። “
– ” የህወሓት አመራር 99.99 በመቶ ጥፋት ገና አልተጋለጠም። “
– ” የህወሓት አመራር ሙሉ በሙሉ ከትግራይ ህዝብ ጫንቃ መውረድ አለበት ፤ የትግራይ ህዝብ በማስያዝ መቋመር ይብቃ። ይህ እስኪቀየር ደግሞ ያለ መታከት እታገላለሁ። “
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
