በኢትዮጵያ በየዓመቱ የትንባሆ ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ የመጣ ሲሆን አምስት በመቶ የሚሆኑ ሰዎች የትንባሆ ተጠቃሚዎች እንዳሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ።በኢትዮጵያ በዓመት 16 ሺ 800 ሰዎች በትምባሆ ምክንያት ህይወታቸው እንደሚያልፍ ተነግሯል።
በተለይ ወጣቶችና የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ዜጎች ለችግሩ ያላቸው ተጋላጭነት የጎላ በመሆኑ ጤናማ ዜጋን ለመፍጠር ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የምግብና የጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
በትምባሆ እና በኒኮቲን ምርቶች ላይ የትምባሆ ኢንዱስትሪ ስልቶችና ጭምብሎችን ማጋለጥ” በሚል መሪ ቃል የአዲስ አበባ ከተማ ምግብ መድሃኒት ባለስልጣን ሜይ 31 የዓለም ትምባሆ የማይጨስበት ቀን በማስመልከት ከተማ አቀፍ የፀረ-ትምባሆ ንቅናቄ ከሚያዚያ 25 እስከ ግንቦት 23/2017 ዓ.ም በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ትምባሆ በየዓመቱ ከ8 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን እንደሚገድል እና ከነዚህ ውስጥ 1.3 ሚሊዮን የሚሆኑት ሳያጨሱ የሚጨስባቸው ሰዎች እንደሚገኙበት ጥናቶች ይጠቁማሉ።
