ታይዋን ለቻይና የሰላም ጥሪ ማቅረቧ ተገለጸ፡፡ የታይዋን ፕሬዝደንት ላይ ችንግ ለቻይና ከሰላም ጥሪ ባቀረቡበት ወቅት ጦርነት ለማንም እንደማይበጅ አመልክተዋል።
ፕሬዝደንቱ በቀጠናው ወታደራዊ አቅምን ማጎልበት ተገቢ እንደሆነም አንስተዋል።
ቻይና በአንጻሩ ላይ ቺንግ ከፋፋይ ናቸው በማለት የሚያቀርቡትን የሰላም ጥሪ ችላ ስትል ቆይታለች።
ቻይና የታይዋንን ክብር እስካከበረች ድረስ ሰላማዊ ግንኙነት ማድረግ እና መተባበር ትፈልጋለች ብለዋል።
ታይዋን ከአሜሪካ ጋር የምታደርገውም ግንኙነት በቻይና በስጋት የሚታይ እንደሆነም የሚነገር ነው።
የቻይና መከላከያ ባለፈው ሳምንት ይፋ እንዳደረገው ታይዋን ቀጠናው መቃቃር ውስጥ እንዲገባና እንዳይረጋጋ እያደረገች ነው በማለት መውቀሱን የዘገበው ሮይተርስ ነው።
