የሆነው ሆኖ በኢትዮጵያ የፀጥታ ችግር አለመቀረፉ እና ተያያዥ ጉዳዮች ካልተፈቱ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ሥርዓት ለውጥ ስጋት አለው ሲባል ምን ማለት ነው?
የሆነው ሆኖ የአለም የገንዘብ ድርጅት የኢትዮጵያ የፀጥታ ችግሮች አለመፈታቱ፣ በትይዩ ገበያውና በመደበኛው የምንዛሪ ዋጋ መካከል ልዩነቱ እየሰፋ መሄዱ፣ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ወደኋላ ሊመልሰው ይችላል የሚለውን ስጋት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተረዳው እንዴት ነው?
የባንኩ ገዢ ማሞ ምህረቱ የአለም የገንዘብ ደርጅት ሪፖርት የኢትዮዽያ ኢኮኖሚ በፍጥነት ማደግ፣ የዋጋ ግሽበት እየረገበ መሄድ፣ የውጪ ምንዛሪ ፍሰት መጨመር እና በትክክለኛው የእድገት ጎዳና ላይ እንደሚገኝ የሚያመላክት ነው ብለዋል።
እሳቸው ይህን ይበሉ እንጂ እንደውም ኢትዮጵያ በገበያው የወሰነችው የውጭ ምንዛሪ እየሰፋ ድጋሚ ከትይዩ ገበያው ጋር አቀራረቡት መባሉ አይቀርም ለዚህም በቶሎ ማሻሻያዎችን ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ የፋይናንስ ምሁራን ይሞግታሉ።
አብዱልመናን መሀመድ(ዶ/ር) በባንክ በፋይናንስ፣ በአካውንቲንግና ኦዲት ስራ ላለፉት 25 ዓመታት በእንግሊዝ ሀገር እና በኢትዮጵያ አገልግለዋል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/4576457457/
ሸገር 102.1
