ኢትዮጵያ ባለፉት 36 ዓመታት ለጅቡቲ የወደብ ኪራይ ያወጣቸው ዶላር የህዳሴ ግድብን የሚያህሉ ከ12 በላይ ግድቦችን የሚያስገነባ ነው ሲሉ ተመራማሪ ሰለሞን ተፈራ ተናገሩ፡፡
በዘርፉ በርካታ ምርምሮችን የሠሩት የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ተመራማሪ አቶ ሰለሞን ተፈራ ለጋዜጣ ፕላስ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ ለወደብ ኪራይ ለጅቡቲ በዓመት ሁለት ቢሊዮን ዶላር ትከፍላለች፡፡
ሀገሪቱ ወደብ አልባ በመሆኗ የገቢና የውጪ ንግድን ለማካሄድ ለወደብ ኪራይ በዓመት ሁለት ቢሊዮን ዶላር ትከፍላለች፤ ባፉት 36 ዓመታትም 72 ቢሊዮን ዶላር ከፍላለች ብለዋል፡፡
ይህም ህዳሴ ግድብን ለመገንባትከወጣው ወጪ አንጻር ሲታይ ሀገሪቱ ባለፉት 36 ዓመታት ለወደብ ኪራይ ያወጣችው ዶላር ቢሰላ ከ12 በላይ ህዳሴ ግድቦችን ማሰራት የሚያስችል ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለወደብ ኪራይ የከፈለችው 72 ቢሊዮን ዶላር ሀገር ውስጥ ኢንቨስት ቢደረግ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ገንብቶ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ይበልጥ ያረጋግጥ ነበር ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለባህር በር የምትከፍለው ዓመታዊ ኪራይና ወደብ አልባ መሆኗ ኢኮኖሚያዊ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እያደረሰባት ነው፤ የባህር በር አልባ መሆን እያስከተለባት ያለውን ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ለመፍታት የተለያዩ ስትራቴጂዎችን ተጠቅማ ወደብ ለማግኘት እየሰራች ነው ሲሉ ጠቁመዋል፡፡
ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እያደረሰባት እና ብሔራዊ የደህንነት ስጋት የደቀነባትን የባህር በር አልባነት ችግር ለመፍታት ካላት ብዙ ሀብት ሰጥታ ለመቀበል እየሰራች ነው፤ እየሰራች ያለውም ስራ የሚበረታታና የሚደገፍ ነው ብለዋል፡፡
ጋዜጣ_ፕላስ
