ቢል ጌትስ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ሀብቱን ለድሃ ሀገራት ለመስጠት ቃል ገባ

Date:

አሜሪካዊ ባለሀብት ቢል ጌትስ ሀብቱን በሙሉ በሚቀጥሉት 2 አስርት ዓመታት ውስጥ ለድሃ ሀገራት ለመለገስ መወሰኑን ይፋ አድርጓል።

በዓለም ቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቷቸው ሊፈቱ የሚገባቸው ብዙ ችግሮች መኖራቸውን የተናገረው ባለሃብቱ፤ እ.አ.አ በ2045 ሀብቱን በሙሉ ለቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በማስተላለፍ ለድኃ ሀገራት የሰብአዊ ዕርዳታ ለመለገስ መወሰኑን አስታውቋል።

ባለሀብቱ በፈረንጆቹ 2000 ከባለቤቱ ጋር በመሆን በቋቋማው ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን አማካኝነት፤ ባለፉት 25 ዓመታት 100 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለግሷል።

ድርጅቱ ባደረገው ድጋፍ በበርካታ ሀገራት የክትባት አቅርቦትን ለማሳደግ፣ የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን ለመከላከል፣ የቲቢ እና የወባ በሽታ ወረርሽኝን ለመቀነስ፣ ገንቢ ሚና ተጫውቷል።

ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን መሥራች ቢል ጌትስ የፋውንዴሽኑን 25ኛ ዓመት ምሥረታ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ “እኔ ከሞትኩ በኋላ ሰዎች ስለ እኔ ብዙ ነገር ሊናገሩ ይቻላሉ፤ ነገር ግን የዓለማችን ቱጃር ቢል ጌትስ አረፍ የሚለው ንግግር ግን አይኖረም፤ ምክንያቱም በህይወት እያለሁ ሀብቴን በሙሉ ለድሆች ዕርዳታ ለመስጠት ወስኛለሁና” ብሏል።

ቢል ጌትስ በዓለም አቀፍ ደረጃ በፖሊዮ፣ በወባ፣ በኩፍኝ አማካኝነት የሚከሰቱ የእናቶችንና የጨቅላ ህፃነትን ሞት ለማስቀረት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።

የ69 ዓመቱ የማይክሮ ሶፍት ኩባንያ መሥራች እና ባለቤት ቢል ጌትስ አሁን ያለው አጠቃላይ ሀብት መጠን 108 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሲሆን ከ20 ዓመታት በኋላ 200 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሚደርስ ይጠበቃል።

ለሰብዓዊና ለበጎ ተግባራት ድጋፍ በማድረግ የሚታወቀው ቢል ጌትስ እ.ኤ.አ በ2026 በዓለም ለጤና ዘርፍ የሚሰጠው ድጋፍ እስከ 9 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይደርሳል።

ባለሃብቱ ከፈራው ሀብት ውስጥ 1 በመቶውን ብቻ በማስቀረት በ20 ዓመታት ውስጥ 99 በመቶውን ለድሃ ሀገራት ለመለገስ መወሰኑን ገልፆ፤ ውሳኔው ሃብታም ሀገራት ለድሃ ሀገራት ይሰጡት የነበረውን ድጋፍ ማቆም በመጀመራቸው ነው ብሏል።

እንደቢዝነስ ደይሊ ዘገባ ቢል ጌትስ የሜሊንዳ እና ጌትስ ፋውንዴሽን በ2045 ስራውን እንደሚያቆም ጠቅሶ፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ የድጋፍ ስራውን በፍጥነት ለማከናወን እንደሚጥር ተናግሯል። 

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

መረጃ በማይሰጡ ኃላፊዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ የሚያስችል ሕግ ተዘጋጀ

የመገናኛ ብዙሃን እና የመረጃ ነፃነት የየራሳቸው ባህሪ ቢኖራቸውም እስካሁን...

የ30 ዓመታትን ጉዞ የሚዘክረው ዳሸን ኤክስፖ

የዳሸን ባንክን 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው...

‹‹ሀገር ጥለው የጠፉና ድርጅቶቻቸውን ለመዝጋት የተገደዱ አሉ››

አቶ አለማየሁ ከተማ(የኢትዮጵያ ሪልስቴት አልሚዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት) ግዮን መጽሔት :-...

የሰላም ስምምነት ሳይፈጸም የንግድ መርከቦች ጉዞ እንደማይጀምሩ የነዳጅ ጫኝ ኩባንያ ኃላፊ ተናገሩ

የሲውዲን ነዳጅ አጓጓዥ ኩባንያ የሆነው ‘ስቴና በልክ’ ዋና ስራ...