ዩኒቨርሲቲው የሰው ኃይል ስምሪት፣ ሃብት የማመንጨት አቅም፣ አስተዳደራዊ መዋቅርና መሰል ተግባራትን ያካተተ ውስጣዊ ግምገማ በማድረግ ውጤቱን ለትምህርት ሚኒስቴር መላኩን የተቋሙ ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ለአገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
ይህን ተከትሎ ተቋሙ ከትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጠው ፈቃድ መሠረት የራስ ገዝነት አሠራሩን ተቀብሎ ተግባራዊ እንደሚያድርግ ገልፀዋል፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በምርምርም፣ በመማር ማስተማር፣ በቴክኖሎጂ ፈጠራና በማኅበረሰብ አገልግሎት ተመራጭ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ ለመዝለቅ የሚያስችል የተሟላ ዝግጅት ማድረጉንም ጠቅሰዋል።
