አዋሽ ባንክ 25.6 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን አስታወቀ!

Date:

አዋሽ ባንክ በ2017 የበጀት ዓመት በግል ባንክ ታሪክ ከፍተኛ የተባለውን 25.6 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡን እና አጠቃላይ የሃብት መጠኑም 442.6 ቢሊዮን ብር መድረሱን ይፋ አድርጓል።ባንኩ ይህን ያስታወቀው ቅዳሜ ዕለት ባካሄደው የባለአክስዮኖች 30ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጉባኤ እና 18ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነው።

በጉባኤው የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፀሐይ ሽፈራው እንዳሉት፣ ባንኩ በሂሳብ ዓመቱ 25 ነጥብ 67 ቢሊየን ብር ያልተጣራ ትርፍ አስመዝግቧል። ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 137 በመቶ እድገት ማሳየቱንና ከፍተኛ ትርፍ መሆኑን መግለጻቸውን ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።

በተጨማሪም የባንኩ ጠቅላላ ተቀማጭ 358 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር መሆኑን ገልጸው ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 125 ነጥብ 9 ቢሊየን እድገት ማሳየቱን ጠቁመዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ባንኩ በሂሳብ ዓመቱ ከ2 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማግኘት መቻሉንና የተሰጠ የብድር ክምችትም 20 በመቶ እድገት ማስመዝገቡንም ተናግረዋል።

የባንኩ የተከፈለ ካፒታል 27 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ደርሷል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው፤ ይህም ብሄራዊ ባንክ ነባር ባንኮች በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሊደርሱበት ይገባል ብሎ ካስቀመጠው የካፒታል መጠን የሚበልጥ መሆኑን አስረድተዋል።

ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ረገድ 600 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓልም ነው ያሉት።አዋሽ ባንክ ከ15 ሚሊየን በላይ ደንበኞች ማፍራቱ እና የቅርንጫፎቹን ቁጥር 989 መድረሱ ተመላክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...