ባካሪ ሳኛ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በመገኘት ውይይት አድርጓል

Date:

የቀድሞው የአርሰናል፣ ማንቸስተር ሲቲ እና ፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ባካሪ ሳኛ ወደ አዲስ አበባ መምጣቱ የሚታወቅ ሲሆን በፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት ተገኝቶ ልምዱን አካፍሏል።

ሳኛ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን ጋር ባደረገው ውይይት ፌዴሬሽኑ በወጣቶች እግር ኳስ ልማት ላይ ሊሰራቸው ስለሚገቡ ሥራዎች እና ልንከተለው በሚባው ተሰጥኦን በለጋ እድሜ የመለየት ሂደት ዙርያ ያተኮረ ሲሆን ሳኛ ባቋቋመው የወጣቶች እግር ኳስ ልማት ተቋም ተሰጥኦ ልየታ (talent identification) በምን መልኩ እንደሚከናወን ገለጻ አድርጓል። በእግር ኳስ ህይወቱ ካሳለፈው ልምድ በመነሳትም ወጣቶች ሊቀስሙ ስለሚገባቸው ጉዳዮች ልምዱን አጋርቷል።

ባካሪ ሳኛ በቆይታው ማብቂያ ባሕላዊ ልብስ እና የፌዴሬሽኑ ብራንድ የሆነው ሀገሬ ኳስ በማስታወሻነት ተበርክቶለታል።

(© EFF)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...