በሁለት ዓመት ውስጥ ከ150 በላይ ኦርቶዶክሳውያን በአንድ ወረዳ ብቻ መገደላቸውን ያልሰማው የሃይማኖት ተቋም።
ጥናቱ የተካሄደው ችግሩን ለይቶ መፍትሔ ለማምጣት ወይስ ሃይማኖት ለመለየት?
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ሪፖርት ስጠብቀው ነበር።
የጠበቅሁት ግን ከዚህ በፊት ከነበረው በተለየ ደፈር ብሎ የኦርቶዶክሳውያንን መከራ ተሰምቶት ይጮሃል ብዬ አይደለም።
የሃይማኖት አባቶችን የያዘ ተቋም እንደመሆኑ እውነት ይመራዋል ፍትሐዊነት ይገልጠዋል ብለን የምንመኘው ቢሆንም Political correctness የሚያስጨንቀው ተቋም እንደሆነ ይታወቃል።
የጠበቅሁት የሰሞኑን የአርሲው ግድያ በተከታታይ ቀናት የሆነ የሩቅ ሳይሆነ የዕለት ነበርና መረጃ ተሰወረብኝ ማለት አይችልም ወይም እድሜ ለቴክኖሎጂ በምስል አስደግፎ መረጃ ይሰጣልና ጥናቱን መሳሳት አይችልም ከማለት ነበር።
እኛ የጥናቱ ቀን አጠረ ለዓመታት የደረሰን በደል ከሳምንት በታች ባለእድሜ የችግሩን መነሻ፣ መጠን እና መፍትሔ እንዴት ያሳያል ስንል የመጀመሪያ ነው ተባለ። እሽ እንደመነሻ ከሆነ እሳት ለማጥፋት እንኳ ቢያንስ የደረሰውን መከራ ሳይፈራ በቁጥር እና በአይነት ይመሰክራል ሲባል የአንድ ሃይማኖት ወይ የአንድ ብሔር አለመሆኑን ደርሼበታለሁ አለ። ይገርማል! የማኅበራዊ ሚዲያ ጫና ሲበረታ እንቅፋት እስኪመታችሁ ላጠና ነው ብላችሁ የሮጣችሁት ለዚህ ነበር?
ይሁን አስቀድሞ በነበሩ መረጃዎችም እንደሰማነው የሌላ ቤተ እምነት ተከታዮችም ተገድለዋል።
እኛ ኦርቶዶክሳውያን ጥያቄያችን ግን ይህ ነበር።
1- ሌሎች ስለተገደሉ እናዝናለን እንቃወማለን። ነገር ግን የኦርቶዶክሳውያን ሞት በንፅፅር የሚገለፅ ሳይሆን ተመርጠው፣ በማእተባቸው ተለይተው የሞቱ ናቸው። ይህ በቤተ ክርስቲያኗ መዋቅር በሀገረ ስብከቱ በኩል በሰበካ ጉባኤ የቀደሙ ዓመታዊ ሪፖርቶችም የተገለጸ ነው። ዛሬም እዛው ያሉ ምእመናንን የሚናገሩት ይህንኑ ነው። ይህንን ደፍራችሁ መናገር ለምን አቃታችሁ? ብትናገሩስ የምታስከፉት ማንን ነው?
2- እነሱ ሃይማኖት ለይተው አልገደሉም ብላችሁ የገዳዮችን ሃጢያት ለማቅለል ምን አስጨነቃችሁ?
ቁጥር ንፅፅር ከጀመራችሁ አይቀርስ ቢያንስ ኦርቶዶክሳውያን በብዛት፣ ያለማቋረጥ እየተገደሉና እየተሰደዱ ስለመሆኑስ ለምን አልገለጻችሁም?
ይህንን ጥናት ተብዬ የፕሮፖጋንዳ ድረታ በመናገራችሁስ በእርግጥ ማንን ነው ምትጠቅሙት? መንግስትን? አይመስለኝም!
የትኛውንስ ሃይማኖት ተከታይ ለመጥቀም ነው? እንጃ! ማንም ሰው የተባለ በዚህ ሥራችሁ አይጠቀምም።
ስለዚህ ዝም በሉ። እንደለመዳችሁት አንዴ ሸራተን አንዴ የሆነ ቅንጡ ሆቴል እየፈለጋችሁ ስብሰባ እና ስልጠና እያላችሁ ተገባበዙ።
ለዚህ ሁሉ በር ከፋቹ አሁንም የእኛው ቤት መሆኑ አይረሳ። ደግሞ አብረው ለመግለጫ ሚቀመጡት ነገርስ?
ከጋዜጠኛ መስከረም ጌታቸው
