አዲስ አበባ ከተማ 232 ኪሎ ሜትር የመልሶ ግንባታና የማስፋፊያ ስራ ተጠናቀቀ

Date:


በአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥን በእጅጉ የሚቀርፍ 232 ነጥብ 84 ኪ.ሜ የሚረዝም የነባር ኤሌክትሪክ መስመሮች የመልሶ ግንባታና የአዲስ መሰረተ ልማት ማስፋፋያ ስራ በተገባደደው የመጀመሪያ ሩብ ዓመት መጠናቀቁን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአዲስ አበባ ሪጅን ኦፕሬሽን ኮርዲኔሽን ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

ከተከናወነው የኤሌክትሪክ መስመር መልሶ ግንባታና የማስፋፊያ ስራ 105 ነጥብ 38 ኪሜ የነባር ኤሌክትሪክ መስመር የመልሶ ግንባታና የአቅም ማሳደግ ሲሆን፤  127 ነጥብ 46 ኪ.ሜ ደግሞ የአዲስ መስመር ማስፋፋያ ይገኝበታል፡፡

ከፍተኛ የሆነ የኃይል ፍላጎት ባለባቸው አካባቢዎች የ130 ትራንስፎርመሮችን አቅም በማሻሻል፣ 210 አዳዲስ ትራንስፎርመሮችን በመትከል ለከተማው አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖርና የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ የሚያስችሉ ስራዎችም በሩብ ዓመቱ ተሰርቷል፡፡

3 ሺህ የሚሆኑ ለኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ምክንያት የሆኑ ግኝቶች ላይ የማስተካከያ (የቅድመ ጥገና) ሥራ ለመስራት ታቅዶ፤ በ2 ሺህ 914 ግኝቶች ላይ የማስተካከል (የቅድመ ጥገና) ሥራ ተከናውኗል፡፡

በአዲስ አበባ ካሉት 36 መጋቢ የምድር ስር ተቀባሪ መስመሮች መካከል 24 የምርመራ ስራ ተሰርቶላቸው ጥገናቸው የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ 12 መጋቢ መስመሮች በሁለተኛው ሩብ ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ከትራንስፎርመሮች ምርመራ ጋር በተያዘዘ የሩብ ዓመቱ መባቻ ድረስ 13 ሺህ 205 ትራንስፎርመሮችን ለመመርመር ታቅዶ ፤ 12 ሺህ 702ቱ ላይ ምርመራ ተደርጎ የጥገና ስራዎቹ በመሰራት ላይ ይገኛሉ፡፡

የአዲስ አበባ ሪጅን ማስተባበሪያ 31 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎችን (ሰብስቴሽን) ተጠቅሞ በተለያዩ የታሪፍ መደብ ያሉ ከ1 ሚሊየን 55 ሺህ በላይ ለሆኑ ደንበኞች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...