በትግራይ ክልል የትምህርት ዘርፉ ለከፋ አደጋ ተጋልጧል

Date:

በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመታት ከተካሄደው ጦርነት በኋላ በትምህርት ዘርፉ የተመዘገቡ “መጠነኛ ለውጦች” በፌደራል መንግስት በጀት እገዳ ምክንያት በጦርነቱ ወቅት ወደነበሩበት የመመለስ ከፍተኛ አደጋ እንደተጋረጠባቸው የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ።

ትምህርት ቢሮው ይህንን ያሳወቀው በአስቸኳይ የገንዘብ እርዳታ ጥያቄ በጻፈው ደብዳቤው ነው። አዲስ ማለዳ የተመለከተችው ደብዳቤ ለትምህርት ሚኒስቴር፣ ለፌደራል እና ለክልሉ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን፣ ለትግራይ ክልል እና ብሔራዊ ትምህርት ክላስተር በየካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጡት የጠየቀበት ነው።

በክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ኪሮስ ግዑሽ(ዶ/ር) የተፈረመው ደብዳቤ በጀት ማቋረጡ በተባበሩት መንግስታት የህጻናት መብቶች ስምምነት እና የዘላቂ ልማት ግቦች ላይ የተቀመጡትን “የህጻናትን የትምህርት መብት በቀጥታ የሚጥስ ነው” ሲል አስታውቋል። በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ድጋፍ ከጦርነት በኋላ የተገኙ ውጤቶችን የሚያጠፋ እና በትግራይም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች ያለውን የረዥም ጊዜ መረጋጋት አደጋ ላይ የሚጥል ነው ሲል ኮንኖታል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ “በተለያዩ ምክንያቶች የተገኙ ለውጦች አሁን ላይ ከፍተኛ አደጋ ተጋርጦባቸዋል” ያለ ሲሆን ከጥቅምት 2018 ጀምሮ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል የተመደበውን የፌደራል በጀት ድጎማ አግዶ እንደሚገኝ አስታውቋል። በዚህም ምክንያት በአሁኑ ወቅት “የመምህራንን ደመወዝ መክፈል አልቻልኩም” በማለት መምህራኑ በጦርነቱ ወቅት የደረሰባቸውን ተቋቁመው ለዚህ መዳረጋቸው ተገቢ አይደለም ብሏል።

ቢሮው በደብዳቤው ላይ እንደገለጸው ከዚህ ቀደም ለ16 ወራት ያክል ያልተከፈለ የደመወዝ እዳ ጋር ተደምሮ መምህራን እና ቤተሰቦቻቻው ለከፋ ችግር ተዳርገዋል ሲል ነው ለተጠሪ ተቋማት ያሳወቀው።
ቢሮው በተጨማሪም ብዙዎቹ መምህራን አሁን ላይ የቤት ኪራይ መክፈል፣ ቤተሰቦቻቸውን መመገብ፣ መሰረታዊ መድኃኒቶን መግዛትም ሆነ መሟላት የማይችሉበት ደረጃ የደረሱ ሲሆን ትምህርት ቤቶችም የመዘጋት አደጋ በስፋት እንዲጋረጥባቸው አድርጓል ነው ያለው።

የክልሉ የትምህርት ሂደት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኋላም በጦርነት የደረሰበት ጉዳት በሚገባ ማገገም ሳይችል አሁን ደግሞ ይህ መዳረጉ ለሌላ ችግር ይዳርገውል ሲል አስጠንቅቋል። በዚህም የትምህርት ቢሮው የድጋፍ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ድምጽ በማሰማት እና አስቸኳይ የገብዘብ ድጋፍ እንዲደረግለት ጥያቄ አቅርቧል።

ቢሮው ለተቋማቱ ከፌደራል መንግስት እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ያላቸውን ተሰሚነት በመጠቀም የተለመደውን በጀት እንድለቀቅለት ግፊት እንድያደርጉ እና የፕሪቶሪያውን ስምምነት የተገቡ ቃሎችን እንዲከበሩ ጠይቋል፡፡

ትምህርት ቢሮው የመምህራንን ደመወዝ፣ የትምህርት ቤት ስራዎች እና አስፈላጊ የመማሪያ ቁሳቁሶችን ለመሸፈን የሚረዳ ገንዘብ በአስቸኳይ እንዲቀርብለት እና የህጻናት የመማር መብታቸው እንዲጠበቅ አሳስቧል።

ቢሮው በጦርነት ምክንያት በትምህርት ላይ ያደርሰውን ጉዳት ለመቋቋም በትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም፣ በመልሶ ማቋቋም፣በትምህርት ቴክኖሎጂ በመምህራን ድጋፍ እና የልማት ፕሮግራሞች ላይ ድጋፉን የጠየቀ ሲሆን የበጀት መቋረጡ በክልሉ ያለውን የትምህርት ሁኔታ የበለጠ ያወሳስበዋል ሲል አጽዕኖት ሰጥቶ አስጠንቅቋል።

(አዲስ ማለዳ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የዓለም የቡና ገበያ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተገለጠ

በዓለም አቀፍ ደረጃ በቡና አቅርቦት ላይ ተፈጥሮ የነበረው ስጋት...

አሜሪካ የኢራንን የጭነት መርከብን መያዟን አስታወቀች

በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን የዘጋችው...

“ቴዲ አፍሮ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ቀይሮታል!” — ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

በ"ወቸው ጉድ" ፖድካስት ላይ እንግዳ ሆነው የቀረቡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ...