የዛሬ 30 ዓመት ቦሌ ኮምዩኒቲን የለቀቁ ዛሬ ሐምሌ 17 ተሰበሰቡ ተማሪዎች ለቀድሞ መምህራን የ 50000ብር የአክሲዮን ስጦታ አበረከቱ
የዛሬ 50 ዓመት በይፋ የተመሠረተው ቦሌ ሕብረተሰብ 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በልዩ ልዩ መንገድ እያከበረ ይገኛል፡፡
በ1987 ዓ.ም ከቦሌ ሕብረተሰብ 8ኛ ክፍል ያጠናቀቁ የቀድሞ ተማሪዎች ከቦሌ የለቀቁበትን 30ኛ ዓመት ዛሬ ሐምሌ 17 2017 በልዩ ሁኔታ አክብረዋል።
የቀድሞ ተማሪዎቹ ሐምሌ 17 2017 ጠዋት ላይ በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ የተገኙ ሲሆን የዛን ጊዜውን ትዝታ ለመቀስቀስ በሚል እንደ ልጅነታቸው ሰልፍ ተሰልፈዋል።
የቀድሞ መምህራን የታደሙ ሲሆን የችግኝ መትከል ሥነ ሥርዐትም ተደርጓል፡፡ እነዚሁ ተማሪዎች ፣አሁን ለደረሱበት የቁምነገር ደረጃ ላበቋቸው መምህራን ዕውቅና የሰጡ ሲሆን መምህራንም ትዝታቸውን እንዲያወሩ ተደርጓል፡፡
የቦሌ ህብረተሰብ 50ኛ ዓመት አከባበር አንድ አካል የሆነው ይህ ዝግጅት በዮድ አቢሲኒያም የተከናወነ ሲሆን ልዩ ልዩ ትዝታ ቀስቃሽ ዝግጅቶችም ነበሩ፡፡
ቦሌ ሕብረተሰብ ከዚህ ቀደም በርካታ ተማሪዎችን ለትልቅ ደረጃ በማድረስ የሚታወቅ ተማሪ ቤት ሲሆን መምህራኖቹም ቢሆኑ በማስተማር ተግባራቸው የተመሰከረላቸው ስለመሆኑ ይነገራል፡፡
በዕለቱ በነበረው የምሳ ሥነ ሥርዐት ላይ 11 የቀድሞ መምህራን የታደሙ ሲሆን 45 የሚጠጉ 1987 ባች ተማሪዎችም በመርሀ ግብሩ ላይ ታድመዋል፡፡
በዝግጅቱ ላይ የቦሌ ሕብረተሰብ አመራሮችና የቦሌ ክፍለ ከተማ የትምህርት ፅህፈት ቤት ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በዕለቱ የተገኙ እንደተናገሩት አዲሱ ትውልድ ከቀድሞዎቹ እየተማረ የራሱን ትልቅ አሻራ ማስቀመጥ አለበት፡፡
መሰናዶውን፣ በማስተባበር ትልቅ አሻራ ያኖሩት የቀድሞ ተማሪዎች በ1987 8ኛ ክፍልን ያጠናቀቁ ተማሪዎች ከዚህ የሚከተሉት ናቸው።
ብሌን ባልቻ
ፍፁም ተክለማሪያም
ኢዮስያስ አራጌ
ሉና ድምፁ
ዓለም ከበደ
ዮናስ በዛብህ
ናቫ አምሀ
ዐይናለም አራጋው
ዳንኤል ንጉሤ ናቸው።
