ቼክ በአገር ዉስጥ ማተም እንደሚጀምር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት አስታወቀ

Date:

በቅርቡ ባንኮች የሚጠቀሙበትና ሚስጥራዊነቱን የተጠበቀ ቼክ በአገር ዉስጥ ማተም እንደሚጀምር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት አስታውቋል። በዚህም ሁሉም ባንኮች የሚጠቀሙበትን ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ እና ወጥነት እንዲሁም የራሱ መለያ ኮድ ያለዉ ቼክ በአገር ዉስጥ ለማምረት ድርጅቱ በሂደት ላይ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚዉ ሽታሁን ዋለ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል። በህትመቱ፤ እያንዳንዱ የባንክ ደንበኛ እና ባንክ የራሱ የሆነ መለያ ቁጥር እንደሚኖረዉና ህጋዊነቱን ለማረጋገጥም ቀላል የሆነ ቼክ ለማምረት እቅስቃሴ ላይ መሆናቸዉን ገልጸዋል። ለህትመቱ የሚረዱ አምስት ማሽኖች የሚያስፈልጉ ሲሆን፤ አራቱ አገር ዉስጥ መግባታቸዉ እና አንድ ከጀርመን አገር የሚገባ ማሽንን በመጠባበቅ ላይ መሆናቸዉን ሥራ አስፈጻሚዉ ተናግረዋል። ማሽኑን በስድስት ወራት ዉስጥ ለማስገባት እንደታቀደ እና እስከሚቀጥለው ዓመት ድረስም ህትመቱን ለመጀመር መታቀዱንም አንስተዋል። ለዚህም ድርጅቱ፤ አስፈላጊ የሆነ የመረጃ ልዉዉጥን ከባንኮች ጋር ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም የገለጹ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም በዉጭ አገር የሚከናወነዉ የቼክ ህትመት የአገር መረጃን ወደ ዉጭ እንዲወጣ ያስገደደ እንደነበርም አስረድተዋል። ሆኖም፤ አሁን ላይ ደረጃዉን የጠበቀ የቼክ ህትመት በአገር ዉስጥ ከተከናወነ ይህንን እና ከቼክ ጋር የተያያዙ ወንጀሎችን እንደሚያስቀርም ሥራ አስፈጻሚዉ ጨምረዉ ለራዲዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ንባብ ለህይወት!” ታላቅ የንባብ ሳምንት እና የመጻሕፍት አውደ ርዕይ

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት እና የንባብ ለህይወት...

በኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ጋር ይኖራሉ

በኢትዮጵያ ከ10 ሚልዮን በላይ ሰዎች ከሄፓታይተስ ቢ እና ከ2...

የቶዮታ ኮሮላ መኪና በኤሌክትሪክ ሊመጣ ነዉ

የዓለማችን ግዙፍ የመኪና አምራች የሆነው ቶዮታ፤ እንደ ቴስላ እና...

ኢራንን ለመምታት የዩናይትድ ስቴትስ ጄቶች ከምድሯ ይነሱ እንደነበር እሥራኤል ይፋ አደረገች

የእሥራኤል መከላከያ ሚንሥትር እሥራኤል ካትስ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ጄቶች...