ነገ በአዲስአበባ የሚስተናገደው 18ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር 

Date:

በአዲስአበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ መነሻው እና መድረሻው ያደረገው በጉጉት የሚጠበቀው  18ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር ነገ በታላቅ ድምቀት ይካሄዳል

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የብዙዎችን ቀልብ የሳበው  ሻምፒዮናው በልዩ ድምቀት ለማከናወን ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቀዋል ።

ፌዴሬሽኑ በሻምፒዮናው ዙሪያ ከአሰልጣኞች ፣ቡድን መሪዎች እና አትሌቲክስ ዳኞች ጋር ውጤታማ ውይይት አድርጓል ።

በሻምፒዮናው  ላይ  3 ክልልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እና  21 ክለቦች   የሚካፈሉ  ሲሆን 156 ሴት  እና  389 ወንድ  በድምሩ  535 አትሌቶች በውድድሩ ላይ ይፎካከራሉ ።

የፌዴሬሽኑ የውድድር ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ብስራት ለጥይበሉ እና አትሌት አሸብር ደምሴ በጋራ ውይይቱን መርተውታል ።

ሻምፒዮናው ከጥዋቱ 12:30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በቀጥታ የሚተላለፍ ይሆናል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...