‹‹… ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ፤››

Date:

ዝክረ መምህር ዘላለም ወንድሙ/ወልደሰማዕት!!

‹‹… ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ፤››
(የሐዋርያት ሥራ ፳፤፳፬)፤

መምህር ዘላለም በአዲስ አበባ ከተማ አዘወትሮ ከሚያገግልባቸው አድባራት መካከል የቀዳሚ ሰማዕት ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ አንዱ ነው፡፡

በቀደመው ጊዜ በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ የሰኞ እለት የሰርክ ጉባኤ የወንጌል የሚያስተምረው እርሱ ነበር፡፡ በኋላ ላይ ግን በአገልግሎት መብዛት የተነሳ የጊዜ መጣበብ ሲገጥመው በወር አንድ ጊዜ በቅዱስ እስጢፋኖስ ወርኻዊ በዓል በዐውደ ምሕረቱ ለወንጌል አገልግሎት አይቀርም ነበር፡፡

ታዲያ በወቅቱ ሙስናው፣ ጎጠኝነቱና ሌብነቱ በየአድባራቱና ገዳማቱ የገነነበት ጊዜ ነበርና መምህር ዘላለም ይህን የሥነ-ምግባር ዝቅጠት፣ የሞራል ንቅዘት እያነሳ አብዝቶ ተግሣጽ አዘል ትምህርትን ይሰጥ ነበር፡፡

አንድ ወቅት ላይ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ የመምህር ዘላለምን ስብከት አድመጠን ስንወጣ፤ በመምህር ትምህርት/ስብከት በጣሙን የተገረመው አንድ ወንድማችን እንዲህ አለን፤

‹‹ዘላለም፤ እንደቀደሙ የወንጌል አርበኛ የሆኑ አባቶቻችን ለሰው ፊት ማያደላ መምህር ወመገሥጽ የሆነ ሰባኪ ወንጌል ነው… ካስተማሩ አይቀርማ እንዲህ ነው… ግን ግን ዘላለም እነዚህ ሰዎች አይፈራም ማለት ነው እንዴ?! ከቤተክርስቲያን አሊያም ከአገልግሎት ቢያፈናቅሉት፤ ቢያሳዱድትስ እንዲህ በአደባባይ እየገሠጻቸው…›› በማለት እየተገረመ ጠየቀን፡፡

ሌላኛው ወንድማችን እንዲህ ሲል መለሰ፤

የቤተክርስቲያን ብርሃን፣ የወንጌል አርበኛ የሆነው አባታችን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፤

‹‹የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ፤›› እንዳለ መምህር ዘላለምም ስለወንጌል አገልግሎት በነፍሱ የቆረጠ አገልጋይ ነው፡፡

እርሱ እኮ ከቤተክርስቲያን አሊያም ከቤተክህነቱ ተቋም አንዳንች ደመወዝ ሆነ የሚያገኘው ድርጎ/አበል የለውም፤ እናም ቀለብ የሚስፍሩለትን ኪሱን የሚሞሉለትን ሰዎች ፊትና እጅ እያየ አይደለም አገልግሎቱ፡፡ እርሱ ወንጌልን በጓዳ፣ በእልፍኝና በአደባባይ እንደሚሸቃቅጡት እንደ አንዳንዶቹ የዘመናችን ምንደኞች ዓይነት አገልጋይ አይደለም፤ 

የእርሱ የአገልግሎት ማእከል ጌታችንና መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ፣ መስቀሉ፤ ቅድስት ቤተክርስቲያ ናት!! በማለት ስለመምህር ዘላለም ምስክርነቱን ሰጠን፡፡ በእውነትም መመህር ዘላለም በቃልም በተግባርም/በሕይወቱ ወንጌልን ሰብኮ ያለፈ፣ ለአምላኩ የታመነ አገልጋይ ነው፡፡ 

ብርሃነ ዓለም፣ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለጥንቷ የኤፌሶን ቤ/ክ ሽማግሌዎች/ቀሳውስት ባስተላለፈላቸው የስንብት ቃል- ለወንድማችን መምህር ዘላለም/ወልደሰማዕት የተከተብኳትን አጭር ማስታወሻ ልቋጭ ወደድኹ፡፡

‹‹… ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ፡፡

ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ፤ አሁንም ለእግዚአብሔርና ያንጻችሁ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ይሰጣችሁ ዘንድ ለሚችል ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ፡፡
ከማንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤ እነዚህ እጆቼ በሚያስፈልገኝ ነገር ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት እንዳገለገሉ እናንተ ታውቃላችሁ፡፡

እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ፤ይህንም ብሎ ተንበርክኮ ከሁላቸው ጋር ጸለየ፡፡

ሁሉም እጅግ አለቀሱ፥ ጳውሎስንም አንገቱን አቅፈው ይስሙት ነበር፤ ይልቁንም ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን አታዩም ስላላቸው ነገር እጅግ አዘኑ፤ እስከ መርከብም ድረስ ሸኙት፡፡
(ሐዋ. ሥራ ምዕ. ፳፤፲፯-፴፰)

መምህር ዘላለም/ወልደሰማዕት የአባቶቻን አምላክ ነፍስህን በአብርሃም እቅፍ ያኑርልን!!

በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...