ኢትዮጵያ በሆቴል ግንባታ ፍጥነት ከአፍሪካ ቀዳሚዎቹ ተርታ ተሰለፈች

Date:

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ደረጃ ከፍተኛ የሆቴል ግንባታ እንቅስቃሴ ከሚታይባቸው ጥቂት አገራት መካከል አንዷ መሆኗን አዲስ ሪፖርት አመለከተ። በሪፖርቱ መሠረት በአገሪቱ ከታቀዱት አዳዲስ የሆቴል ክፍሎች ውስጥ 80 በመቶ የሚጠጉት በአሁኑ ወቅት በግንባታ ላይ ይገኛሉ።

በደብሊው ሆስፒታሊቲ ግሩፕ የቀረበው ይህ ሪፖርት፤ ኢትዮጵያ በ34 ሆቴሎች ውስጥ 5,964 ክፍሎችን ለመገንባት በሂደት ላይ መሆኗንና ይህም በአህጉሪቱ አምስተኛ ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጣት ገልጿል። ከእነዚህ ውስጥ 4,768ቱ (79.9%) በግንባታ ላይ ናቸው። ይህም ኢትዮጵያን ከአፍሪካ 10 ግዙፍ ገበያዎች መካከል ከኬንያ ቀጥላ በግንባታ እንቅስቃሴ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ያደርጋታል።

ይህ በግንባታ ላይ ያተኮረው እንቅስቃሴ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገነቡ አዳዲስ ሆቴሎች በዕቅድ ደረጃ ላይ ካሉ ሌሎች የአፍሪካ ገበያዎች በበለጠ ፍጥነት ለአገልግሎት ዝግጁ እንደሚሆኑ ያሳያል።

ጥናቱ በመጪው መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም. በናይሮቢ በሚካሄደው “የወደፊቱ የአፍሪካ ሆስፒታሊቲ ጉባኤ” ላይ በዝርዝር ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...