ንጋት የበጎ አድራጎት የተራድኦ ድርጅት ለችግር የተጋለጡ ማህበረሰቦችን ለመደገፍ ከግንቦት 16 እስከ 20 የገቢ ማሰባሰብያ ፕሮግራም ሊያካሂድ መሆኑን ተገልጿል።
ንጋት የበጎ አድራጎት ድርጅት ሰው መርዳት ሰው የመሆናችን ማሳያ ነው በሚል ቃል አቅመ ደካማ ወገኖችን በ መርዳት እና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ በመስጠት ላይ ይገኛል::
ንጋት በጎ አድራጎት ተራድኦ ድርጅት በአቶ ንጋቱ አስፋ የተመሰረተ ሲሆን ህጋዊ ፍቃድ አግኝቶ ወደ ስራ ከገባ 8 ወራት አስቆጥሯክ አሁን ላይ 84 ዜጎችን ከጎዳና በማንሳት ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።
ንጋት የበጎ አድራጎት ድርጅት ከ ግንቦት 16- 20 /2017 ድረስ የሚቆይ የ ገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር አዘጋጅቷል::
የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሩ በቲክቶክ እና በዩቲዩብ በቀጥታ ስርጭት ለአራት ቀናት በተከታታይ እንደሚካሄድ ተነግሯል።
ሆኖም በዚ መልካም ተግባር ላይ መሳተፍ እና ማገዝ ለሚፈልጉ ሁሉ ቤታችን ክፍት ነው ብለዋል::
የገቢ ማሰባሰብያ መርሃ ግብሩ አላማ ድርጅቱ ለተቸገሩ ግለሰቦች እና ቤተሰቦች የሚደረገውን ድጋፍ ለማጠናከር ነው ተብሏል።
የተራድኦ ድርጅቱ አቅመ ደካሞችን ከጎዳና እንዲነሱ በመርዳት፣ የቤት ኪራይ በመሸፈን፣ ምግብ በማቅረብ እና የጤና ችግር ያለባቸውን ወገኖች ለመርዳት ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል።
በገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሩ ላይም የቀራፂ እና ሰዓሊ ግሩም ስራዎች በጨረታ እንደሚሸጡ በመግለጫው ላይ ተገልጿል።
