በጋምቤላ ክልል   ከ 42 ሺህ በላይ ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተነገረ

Date:

በክልሉ ሰብአዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸዉ  ከ 42 ሺ በላይ ዜጎች በጎርፍ እና በግጭት ምክንያት ተፈናቅለዋል።

በጋምቤላ ክልል ያሉ የሰብአዊ  ተራድኦ ድርጅቶችም የተደራሽነት ችግር አጋጥሟቸዋል ተብሏል።

የተራድኦ ድርጅቶቹ የሰብአዊ ድጋፍን በተቀናጀ መልኩ ለማሰራጨት ማስተባበር ላይ ክፍተት እንዳጋጠማቸው ሰምተናል።

የጋምቤላ ክልል የአደጋ ስጋት  ስራ አመራር አገልግሎት ዳይሬክተር ጃክ ጆይ እንደገለፁት ድርጅቶቹ በሚጠበቀዉ መጠን እየሰሩ አለመሆኑን ገልፀዋል።

በተለይም እነዚህን የሰብአዊ ተራድኦ ድርጅቶች የሚያስተባብራቸዉ ተቋም የ ተመድ የሰብአዊ ማስተባበሪያ ኦቻ ሲሆን ቢሮዉ  ጋምቤላ ከተማ ላይ አለመሆኑ አንዱ ምክንያት እንደሆነ አንስተዋል።

ቢሮዉ መገኛዉ አሶሳ ላይ በመሆኑ ተቋማቱን ለሰብአዊ ድጋፍ ለማስተባበር ባለመቻል  ክፍተት እየፈጠረ ስለመሆኑ የጋምቤላ ክልል የአደጋ ስጋት አመራር አገልግሎት ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።

ዳይሬክተሩ በክልሉ  42 ሺህ 374 ሰብአዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸዉ  የጎርፍ እና የግጭት ተፈናቃዩች በክልሉ አሉ ብለዋል።

በክልሉ  ካቢኔ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር  ስትራቴጂክ ኘላን ቢፀድቅም ለተግባራዊነቱ በጀት የማፈላለግ ስራዉን የአለምአቀፍ ተቋማት ያደረጉት  የ ፈንድ  ገደብ እክል ፈጥሯል ሲሉ ገልፀዋል።

ኢትዩ ኤፍም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...

አዲስ አበባ፦ የዜጎች ቀይ መስመር!

(የግል አስተያየት) አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መናገሻ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች ለዘመናት...

አብን የምክክሩን ውጤት ውድቅ አደረገ!

አብን በሀገራዊ ምክክሩ ማጠቃለያ ላይ የተፈጸመውን “ሕገ-ወጥ ጣልቃ-ገብነት” በመቃወም...