አሐዱ ባንክ 22ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን አከበረ

Date:



አሐዱ ባንክ 22ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ትውልድን በሥነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሠራር!” በሚል መሪ ሐሳብ፤ ለባንኩ ከፍተኛ የሥራ  ኃላፊዎች እና ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ የምክክር መርሐ ግብር በባንኩ አዳራሽ አካሒዷል፡፡

የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ በዛ በንግግራቸው እንደገለጹት ሙስናና ብልሹ አሠራር ትውልድን እና ተቋምን የሚጎዳ ስለሆነ፤ አሐዱ፡ባንክ በዕሴቶቹ ድልድይነት እየተከላከለ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል፡፡  ለዚህ ደግሞ ሠራተኞቹና አመራሮቹ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በዕለቱም የፌዴራል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ተወካይ የተገኙ ሲሆን፤ ተወካዩም እንደ ሀገር ወደ ትልቅነት ለመሸጋገር በሥነ-ምግባር የታነጸ ትውልድና  ተቋም እንደሚያስፈልግ በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የሀብት ማሳወቂያ የምዝገባ ሰነድ ርክክብ በማድረግ መርሐ ግብሩ ተጠናቋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምርጫው ራሳቸውን አገለሉ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በኦሮሚያ...

ኢራን ከአሜሪካ ጋር ‹‹ሁሉን አቀፍ ስምምነት›› እንደምትፈልግ ገለጸች

ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ጦርነት ለማቆም ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው...

የሪል እስቴት ዘርፍ ዘመናዊ የክፍያ ቴክኖሎጂን ለማስፋፋት አዲስ አጋርነት ፈጠረ

በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ዘርፍ ግንባር ቀደም ከሆኑት ድርጅቶች አንዱ...

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...