የካሜሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆሴፍ ዲዮን ንጉቴ (ዶ/ር) ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩን እና የካምቴል ዋና ዳይሬክተር ጁዲት ያህ ሳንዴይን አነጋግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዲጂታል ሽግግር ለኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ በመሆኑ የአፍሪካ ኦፕሬተሮች ትብብር ወሳኝነት ገልጸው የኢትዮጵያ የዲጂታል ተሞክሮ በሀገራቸው እንዲተገበር ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ፍሬህይወት ታምሩ በበኩላቸው፤ ኢትዮ ቴሌኮም በመሰረተ ልማት፣ አገልግሎት ተደራሽነት፣ በዋጋ ተመጣጣኝነት እና በፋይናንስ አካታችነት ያካበተውን ልምድ በማካፈል የካሜሩንን የዲጂታል ራዕይ እንደሚያግዙ ገልጸዋል።
ይህ የዲጂታል መሰረተ ልማት ማስፋፋት ኢኮኖሚን ከማነቃቃቱም ባለፈ፣ ትብብሩ ለአፍሪካ ኦፕሬተሮች አርአያ እንደሚሆን አክለው ተናግረዋል።
የካምቴል ዋና ዳይሬክተር ጁዲት ያህ ሳንዴይ፣ የኢትዮ ቴሌኮምን ሀገራዊ የዲጂታላይዜሽን ስኬት በአካል መመልከታቸውን አስታውሰው፣ ይህንኑ ልምድ በሀገራቸው እንደሚተገብሩ አረጋግጠዋል።
ልዑካን ቡድኑ ከካሜሩን የፖስታ እና ቴሌኮሙኒኬሽን እንዲሁም ከሠራተኛ እና ማህበራዊ ዋስትና ሚኒስትሮች ጋርም ተወያይቷል።
Ethiotelecom
