አሜሪካ ከፍተኛ የማጥቂያ መሣሪያዎች ያሏት ቢሆንም በኢራን ላይ የሚከፈተውን አጠቃላይ ጦርነት (የለየለት ጦርነት) ዘመቻ ለረጅም ጊዜ ማስቀጠል አቅሟን ከመጨረሱም በላይ ወሳኝ የሆኑ ወታደራዊ ንብረቶቿ ለጥቃት እንዲጋለጡ ያደርጋል ሲሉ የጦር ዘጋቢው ኤልያስ ጄ ማግኒየር ገልጸዋል።
🟠 አሜሪካ ከፍተኛ ጥቃቶችን ለመሰንዘር የሚያስችል በቂ የተኩስ ኃይል ያላት ቢሆንም በአሜሪካ የጦር ሰፈሮች፣ በአጋሮቿ እና በእስራኤል ላይ ከሚሰነዘሩት የኢራን የአጸፋ ጥቃቶች ለመከላከል የሚያስችሏት የመጥለፊያ ሚሳኤሎች ክምችት ግን ውስን ነው።
🟠 ኢራን ግጭቱን በጂኦግራፊያዊ መልኩ ማስፋት የምትችል ሲሆን፤ ይህም ዋሽንግተን መከላከል ያለባትን የዒላማዎች ቁጥር እንዲጨምርና ፖለቲካዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ መዘዞችን ከፍ እንዲል ያደርጋል።
🟠 ኢራን የጠላትን መከላከያ ሥርዓት በባሊስቲክ እና በክሩዝ ሚሳይሎች በማጨናነቅ፣ አሜሪካ እና አጋሮቿ ውድ የሆኑ የመጥለፊያ ሚሳኤሎቻቸውን በማታለያዎች ላይ እንዲያባክኑ ልታደርግ ትችላለች፤ በዚያው ወቅትም የጦር ሰፈሮችን፣ የሎጅስቲክስ ማዕከላትን፣ ወደቦችን፣ የራዳር ጣቢያዎችን እና የነዳጅ ማከማቻዎችን በትክክል መምታት ትችላለች።
ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ያላት ቁጥጥር ያላትን የድርድር አቅም ይበልጥ ያጎላዋል፡፡ ይህም ዓለም አቀፍ የባሕር ላይ መላላኪያዎችን የሚያሰጋ እና ለማንኛውም የአሜሪካ ወታደራዊ ግጭት ማባባስ የሚከፈለውን ዋጋ እጅግ ከፍ የሚያደርግ ነው።
በፋርስ ባሕረ ሰላጤ እየጨመረ የመጣው የአሜሪካ ወታደራዊ ስምሪት፤ ለከፍተኛ ወታደራዊ ግጭት የሚደረግ ዝግጅት ምልክት ሊሆን እንደሚችል የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ቀደም ብለው ዘግበው ነበር።
