አሜሪካ ጄት ሲያበር የተመታውን አብራሪዋን ታደገች

Date:

አርብ ዕለት በደቡባዊ ኢራን ተመትቶ የወደቀውን የአሜሪካ ተዋጊ ጄት ውስጥ የነበረው የአየር ኃይል አባል መገኘቱን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስታወቁ።

የአሜሪካ ኤፍ-15ኢ ስትራይክ ኤግል ተዋጊ ጄት ኢራን ግዛት ውስጥ ከተመታ በኋላ ሁለቱም አገራት አብራሪዎቹን ሲያድኑ ነበር።

አሜሪካ በዚያው ቀን አንዱን አብራሪ መታደግ የቻለች ሲሆን ሁለተኛውን የአየር ኃይል አባል ለማዳን በጠላት ግዛት ውስጥ አደገኛ የፍለጋ ዘመቻ ስታከናውን ነበር።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዛሬ በትሩዝ ሶሻል ማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ “አግኝተነዋል” ሲሉ ሁለተኛውን አብራሪ መታደግ መቻሉን አስታውቀዋል። ጠፍቶ የነበረው የአየር ኃይል ባልደረባ “ጉዳት ቢደርስበትም” በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

“ላለፉት በርካታ ሰዓታት የአሜሪካ ሠራዊት ከአሜሪካ ታሪክ ውስጥ እጅግ ድፍረት የተሞላበትን የፍለጋ እና የማዳን ዘመቻ አካሂዷል” ብለዋል።

የጠፋው የአየር ኃይል አባል “እጅግ የተከበረ ኮሎኔል” ሲሉ የገለጹት ትራምፕ፤ “በኢራን አደገኛ ተራሮች ውስጥ ከጠላት መስመር ጀርባ ሆኖ፣ በጠላቶቻችን እየታደነ” ነበር ብለዋል።

ይሁን እንጂ የአሜሪካ ኃይሎች “በቀን ለ24 ሰዓታት ያለበትን ቦታ ሲከታተሉ እንደነበር” ጠቅሰዋል። “ጉዳት ደርሶበታል፤ ነገር ግን ደህና ይሆናል” ብለዋል።

ትራምፕ በዚህ ልጥፋቸው እስካሁን ድረስ ከአስተዳደራቸው ይፋዊ ማረጋገጫ ስላልተሰጠበት የመጀመሪያው አብራሪም አንስተዋል።

የመጀመሪያውን “ጀግና አብራሪ” መታደግ ስለመቻሉ ማረጋገጫ ያልተሰጠው “ሁለተኛውን የመታደግ ዘመቻ እያዳያበላሽ” በሚል እንደሆነ አስረድተዋል።

“መቼም ቢሆን አሜሪካዊ ተዋጊን አንተውም” ሲሉም አክለዋል። እንደ ትራምፕ ገለጻ በኢራን ግዛት ውስጥ የማዳን ዘመቻ የተከናወነው “አንድም አሜሪካዊ ሳይገደል ወይም ሳይጎዳ” ነው።

“የጠላት መስመር” ውስጥ የነበረውን አሜሪካዊ ወታደር ለመታደግ “በርካታ አውሮፕላኖች” ተሰማርተው እንደነበረም ተናግረዋል።

አሜሪካ መታደግ የቻለችው አብራሪዋ በኢራን ባለሥልጣናትም ፍለጋ ሲካሄድበት ነበር። የኢራን ጦር አሜሪካዊውን ወታደር ለያዘ ሰው ከ66 ሺህ ዶላር በላይ ሽልማት ማዘጋጀቱን አስታውቆ ነበር።

ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተለቀቁ ቪዲዮዎችም በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢራናውያን በደቡብ ምዕራባዊ ኢራን ወደሚገኘው ተራራማ ቦታ ሲያመሩ አሳይተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የዓለም የቡና ገበያ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተገለጠ

በዓለም አቀፍ ደረጃ በቡና አቅርቦት ላይ ተፈጥሮ የነበረው ስጋት...

አሜሪካ የኢራንን የጭነት መርከብን መያዟን አስታወቀች

በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን የዘጋችው...

“ቴዲ አፍሮ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ቀይሮታል!” — ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

በ"ወቸው ጉድ" ፖድካስት ላይ እንግዳ ሆነው የቀረቡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ...