አሜሪካ-እስራኤል እና ኢራን ጦርነቱን እንዲያቆሙ ጥሪ ቀረበ

Date:

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አሜሪካ እና እስራኤል በጥምረት ኢራን ላይ እያካሄዱ ያለውን ጦርነት እንዲያቆሙ ያሳሰቡ ሲሆን ወታደራዊ እርምጃ በዲፕሎማሲ እንዲተካ ጠይቀዋል።

ጉተሬዝ በብራሰልስ እየተካሄደ ባለው የአውሮፓ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ጦርነት ለማቆም ጊዜው አሁን ነው ብለዋል።

በአሜሪካ እና በእስራኤል የተጀመረው ይህ ጦርነት ከቁጥጥር ውጪ የመውጣት ስጋት እንዳለው እና በንፁሃን ዜጎች ላይ ከፍተኛ መከራ እያደረሰ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ዋና ጸሐፊው አክለውም የጦርነቱ ተፅዕኖ ከጦር ሜዳው ባለፈ እየተስፋፋ መሆኑን ገልጸው፣ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ እያደረሰ ያለው መዘዝ እጅግ አስከፊ ነው ብለዋል።

በተለይም በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ላይ አሳዛኝ ውጤት ሊያስከትል እንደሚችል በማስጠንቀቅ፣ ከጦርነት ይልቅ ዲፕሎማሲ የሚያሸንፍበት ጊዜ አሁን ነው ሲሉም አክለዋል።

የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገራት መሪዎች በመካከለኛው ምሥራቅ ያለው ውጥረት በተለይም በአውሮፓ የኃይል (ኢነርጂ) ዋጋ፣ በኢነርጂ ዋስትና እና በቀጠናዊ መረጋጋት ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ላይ ለመወያየት ነው በብራሰልስ የተሰባሰቡት።

አሜሪካ እና እስራኤል በጥምረት የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም በኢራን ላይ መጠነ ሰፊ ጦርነት መጀመራቸውን ተከትሎ የዓለም የባሕር ትራንስፖርት ተስተጓጉሏል፤ የነዳጅ ዋጋ እንዲንር አድርጓል እንዲሁም የዓለም  ኢኮኖሚ እየተናጋ መሆኑን ሽኑዋ ዘግቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...