ከእስራኤል ጋር በተደረገው የሁለት2 ዓመት ጦርነት አብዛኞቹ መሪዎቹ የተገደሉበት የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሐማስ ባወጣው መግለጫ፣ ኻሊል አል ሃያን አዲሱ መሪው አድርጎ መምረጡን አስታወቀ።
አዲሱ መሪ እስራኤል በጋዛ ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ባካሄደችበት ወቅት የተገደለውን ያህያ ሲንዋርን የሚተኩ ናቸው።
ከስደት በኋላ በጋዛ የነበረውን ንቅናቄ እየመሩ ያሉት ኻሊድ አል ሃያ፣ ከሦስት ዓመታት ገደማ በፊት ከእስራኤል ጋር ከተጀመረው አውዳሚ ጦርነት በኋላ ወደ መሪነት የመጡ አክራሪ አቋም ያላቸው የቡድኑን አባላት የሚወክሉ ተደርገው ይታያሉ።
ሃያ የአንዋር ሲንዋር የቅርብ አጋር የነበሩ ሲሆን፣ ኢራን ውስጥ በእስራኤል ከተገደሉት የቡድኑ የፖለቲካ መሪ ኢስማኤል ሃኒያ ጋር የሚያያዘውን ፖለቲካዊ መስመር የሚያስቀጥሉ ተደርገው ይታሰባሉ።
ሃይያ የሐማስ ዋነኛ ተደራዳሪ በመሆን የቡድኑ ልዑክ ያደረገውን ቀጥተኛ ያልሆነ የተኩስ አቁም ድርድር መርተዋል። በግብፅ እና በኳታር አማካኝነት ከአደራዳሪዎች ጋር በመገናኘትም ዓለም አቀፍ እውቅናን አትርፈዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የሐማስን የዲፕሎማሲያዊ እና የፖለቲካ ዕቅዶችን በመምራት የበለጠ ኃላፊነትን ይዘዋል።
የ65 ዓመቱ ሃያ በዚህ ዓመት መስከረም ላይ በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ውስጥ የሐማስ መሪዎች ስብሰባ ላይ እያሉ ከተፈጸመው የእስራኤል የአየር ጥቃት ተርፈዋል።
በጥቃቱ ወንድ ልጃቸው፣ አምስት ዝቅተኛ ደረጃ ያላቸው የቡድኑ አባላት እና የኳታር የፀጥታ ኃይል አባል መገደላቸው ይታወሳል።
ኳታር ውስጥ የነበሩት የሐማስ መሪዎች ዒላማ የተደረጉት የጋዛ ጦርነትን የቀሰቀሰውን የቡድኑ ጥቃት በመምራታቸውን እንደሆነ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር በወቅቱ አሳውቀዋል።
ዳጉ ጆርናል
