አርሰናል በሜዳው ከአትሌቲክ ቢልባኦ ጋር ያደረገውን የኤምሬትስ ካፕ ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
ለአርሰናል የማሸነፊያ ግቦችን ቪክቶር ዮኬሬሽ ፣ ቡካዩ ሳካ እና ካይ ሀቨርትዝ አስቆጥረዋል።
ከጨዋታው በኋላ በተሰጠ የመለያ ምት አርሰናል 6ለ5 ማሸነፍ ችሏል።
ስዊድናዊው የፊት መስመር አጥቂ ቪክቶር ዮኬሬሽ የአርሰናል የመጀመሪያ ጎሉን አስቆጥሯል።
አርሰናል በቀጣይ የፕርሚየር ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር የሚያደርግ ይሆናል።
