አርሰናል የዮኬሬሽን ዝውውር አጠናቀቀ

Date:

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የቪክቶር ዮኬሬሽን ዝውውር በሙሉ ስምምነት ማጠናቀቁን ዘ አትሌቲክ አረጋገጠ።

መድፈኞቹ ተጫዋቹን በ 63.5 ሚልዮን ዩሮ እና ተጨማሪ 10 ሚልዮን ዩሮ ክፍያ ለማስፈረም ተስማምተዋል።

ስዊድናዊው አጥቂ ቪክቶር ዮኬሬሽ አሁን ላይ የጤና ምርመራውን እንዲያደርግ ከስፖርቲንግ ሊዝበን ፍቃድ ተሰጥቶታል።

ተጨዋቹ በነገው ዕለት ወደ አርሰናል የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ የጤና ምርመራውን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ቪክቶር ዮኬሬሽ በአርሰናል ቤቴ ታሪካዊውን የቴሪ ሄንሪ 14 ቁጥር ማልያ ለብሶ እንዲጫወት እንደተዘጋጀለት ተገልጿል።

@tikvahethsport  

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...