አርሰናል 4ለዜሮ ሲያሸንፍ ማንቼስተር ዩናይትድ ተሸነፈ

Date:

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 33ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል ከሜዳው ውጪ ኢፕስዊች ታውንን ሲያሸንፍ ማንቼስተር ዩናይትድ ሽንፈት አስተናግዷል፡፡

ቀን 10 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ አርሰናል ኢፕስዊች ታውንን 4 ለ 0 አሸንፏል፡፡

አርሰናል የጨዋታ ብልጫ በወሰደበት ጨዋታ ሊያንድሮ ትሮሳርድ (2)፣ ጋብርኤል ማርቲኔሊ እና ኢታን ኒዋኔሪ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

በተመሳሳይ በተደረገ ሌላ ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ በሜዳው ፓብሎ ሳራቢያ ባስቆጠራት ግብ በወልቭስ 1 ለ 0 ተሸንፏል፡፡

ሽንፈቱ ማንቼስተር በውድድር ዘመኑ ያስተናገደው 15ኛ ጨዋታ ሆኖ ተመዝግቧል።

በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገው የቼልሲ እና ፉልሃም ጨዋታ ድራማዊ ትዕይንትን አስተናግዶ በቼልሲ 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

በጨዋታው ፉልሃም በአሌክስ ኢዮቢ ግብ እስከ 84ኛው ደቂቃ ሲመራ ቢቆይም ታዳጊው ትሬቅ ጆርጅ በ85 እንዲሁም ፔድሮ ኔቶ በጭማሪ ደቂቃ ግብ አስቆጥረው ቼልሲ አሸናፊ ሆኗል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...

ኧረ ፋታ ስጡን?!

መንግስት ግን" ምን ሁኑ ?" ሊለን ነው :: አጀንዳ...